የማሕበረሰብ መመሪያ 

የ Premise ዓላማ በዓለም ላይ የትክክለኛ መረጃ ምንጭ መሆን ነው፡፡ የ Premise አፕሊኬሽንን ለመጠቀም አካውንት ሲከፍቱ፣ የዓለም አቀፍ ማህበረሰባችን አንድ አካል ይሆናሉ፡፡ 

ታማኝነት እና መከባበር የ Premise ዋነኛ የማህበረሰባችን መመሪያ እሴቶች ናቸው፡፡ በተጨማሪም ይህ የማህበረሰባችን መመሪያ፣ በጥናቶቻችን ለሚሳተፉ ተሳታፊዎች ሁሉ እንደ መመሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ 

ስለ Premise አጠቃቀም መመሪያ፡ 

በ Premise ጥናቶች ሲሳተፉ፣ ለሚኖሩበት ሃገር እና አካባቢ መሻሻል አስተዋጾ ያደርጋሉ እንዲሁም ደግሞ ለተሳትፎዎ ገንዘብ ያገኛሉ፡፡ የሚከተሉት ነጥቦች የ Premise አፕሊኬሽንን በምን መልኩ መጠቀም እንዳለብዎት ይገልፃሉ፡፡ 

ለጥያቄዎች በታማኝነት መልስ መስጠት 

በጥናቶቻችን አማካኝነት የሚሰጡን መልስ እና አስተያየቶች፣ አካባቢዎን ለማሻሻል ትኩረት በማድረግ ለሚተጉ አጋር ድርጅቶች፣ ካምፓኒዎች እና ኤን.ጂ.ኦዎች ጠቃሚ በመሆናቸው እነዚህ ድርጅቶች በእርስዎ ሃገር እና አካባቢ ያለውን ትክክለኛ ነገር እንዲገነዘቡ እና የበኩላቸውን አስተዋጾ ለማድረግ እንዲችሉ ያግዛቸዋል፡፡ የ Premise ተሳታፊዎች፡ 

  • ለጥናት ጥያቄዎቻችን በተቻለው መጠን በሐቀኝነት መልስ መመለስ አለባቸው፤ 
  • ሆን ብለው የተሳሳተ ወይም የሚያሳስት መረጃ መስጠት የለባቸውም፤ 
  • በጥናቶቻችን ሲሳተፉ ሰዎችን፣ በአካባቢያቸው ያሉ ድርጅቶችን ወይም ተቋማትን ህግ አክብረው ስነ ስርዓት በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት፤ 
  • የ Premise አፕሊኬሽንን መጠቀም ያለባቸው በሞባይል ስልካቸው ብቻ መሆን አለበት፤ 
  • በጥናቶቻችን ሲሳተፉ እና መልስ ሲሰጡ የማንንም እገዛ ሳይጠይቁ፣ ከሌሎች ጋር በጋራ ሳይሰሩ፣ ወይም ደግሞ በግላቸው መሆን አለባቸው፡፡

የ Premise አፕን ሲጠቀሙ የራስን ደህንነት ለመጠበቅ ማድረግ ያለባቸው 

Premise የተሳታፊዎችን ደህንነት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ ስለሆነም በ Premise ጥናቶች ተሳታፊ ከሆኑ፡ 

  • የሃገርዎን ሕግ ማክበር እና አካባቢዎ ለአደጋ የማያጋልጥዎ መሆን ይኖርበታል፤ 
  • ጥናቶችን መስራት ያለብዎት ለእርስዎ ችግር በማይፈጥሩ ቦታዎች ላይ ብቻ ነው፤ 
  • ጥናቶችን ሲሰሩ ሰዎች ከከለከሉዎት ወይም ከቦታው እንዲሄዱ ሰዎች ካዘዙዎት፣ ወዲያውኑ ተግባሩን አቋርጠው ከቦታው መንቀሳቀስ አለብዎት፡፡ 

የሚከለከሉ ተግባራቶች፡ 

በጥናቶቻችን ሲሳተፉ ጨዋነት እና ትክክለኛነት የጎደለው ባሕርይ ማሳየት፣ እንዲሁም የማጭበርበር ድርጊቶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ 

ከአንድ በላይ አካውንት መክፈት ወይም አካውንት በጋራ መጠቀም 

አካውንት በጋራ መጠቀም አይፈቀድም፡፡ ስለሆነም፡ 

  • አንድን አካውንት ከሌላ ሰው ጋር በጋራ መጠቀም አይፈቀድም፤ 
  • ከአንድ በላይ አካውንት እና ስልክ መጠቀም አይፈቀድም (ማለትም አንድ ተሳታፊ መክፈት የሚችለው አካውንት አንድ ብቻ ሲሆን፣ ይህንንም መጠቀም ያለበት በአንድ ስልክ ላይ ብቻ ነው) 
  • ክፍያ የሚያወጡበትን ቁጥር ወይም ኢሜል ያለኛ ፍቃድ ከሌላ ሰው ጋር በጋራ መጠቀም አይቻልም፡፡

ቦታን ሆን ብሎ መቀየር 

በጥናቶቻችን ሲሳተፉ፣ የተጠየቁ ነገሮች የሚገኙባቸውን ትክክለኛ ቦታ መመዝገብ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ስለሆነም ተሳታፊዎች፡ 

  • የተለያዩ ሶፍትዌሮችን ሆን ብሎ በመጠቀም ቦታቸውን መቀየር ወይም ማጭበርበር የለባቸውም፤ 
  • ጥናቱን የሚጀምሩበት ቦታ እና የሚያጠናቅቁበት ቦታ የተለያየ መሆን የለበትም፡፡

ጎጂ የሆኑ ወይም ተገቢ ያልሆኑ ነገሮችን መላክ 

ጎጂ የሆኑ ወይም ደግሞ አግባብነት የሌላቸውን ኢንፎርሜሽኖች ከሲስተማችን ላይ እናስወግዳለን፡፡ ስለሆነም የ Premise ተሳታፊዎች፡ 

  • አስፀያፊ የሆኑ፣ ስነ ምግባር የጎደላቸውን፣ ጋጠወጥነት የሚታይባቸውን፣ የልቅ ወሲብ፣ የጥላቻ፣ ወይም ደግሞ ተቀባይነት የሌላቸውን ማንኛውም አይነት ምስል እና ፅሁፎችን መላክ የለባቸውም፤ 
  • የማስታወቂያ እና የሪፈራል ሊንኮችን መላክ የለባቸውም፤ 
  • ቫይረስ እና ትሮጃን ሆርስ የያዙ፣ ወይም ደግሞ አገልግሎት የማይሰጡ ፋይል እና መረጃዎችን መላክ የለባቸውም፡፡

የተግባር ግምገማ እና ቅሬታ 

የ Premise ተሳታፊዎች በጥናቶቻችን ሲሳተፉ፣ የሚያስረክቡን መልሶች እና ፎቶዎች በሙሉ ይገመገማሉ፡፡ ያስረከቡት ተግባር ካልፀደቀ፣ ለወደፊቱ እንዲማሩበት በማሰብ ውድቅ የተደረገበትን ምክኒያት እንገልፅላቸዋለን፡፡ ተግባሩ ካልፀደቀ እና ተሳታፊው በውጤቱ ካልተስማሙ፣ እንደገና እንዲገመገም መጠየቅ የሚቻል ሲሆን ነገር ግን ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነገሮች መገንዘብ ያስፈልጋል፡ 

  • የጠየቁን ተግባር እንደገና እስከሚገመገም ድረስ ከ 3-5 ቀን ሊወስድ ይችላል፤  
  • ውድቅ የተደረገ ተግባርን እንደገና እንዲገመገም መጠየቅ የሚቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤ 
  • ከተገመገመ 14 ቀን የሆነው ወይም ያለፈው እንደገና አይገመገምም (በውጤቱ ዙሪያ ቅሬታ ካለ፣ ተሳታፊዎች ወዲያውኑ ቅሬታ ማስገባት አለባቸው)፤ 
  • የግምገማ ቡድናችን ተግባሩን እንደገና ገምግመው ውጤት ካሳወቁ በኋላ፣ ውሳኔያቸው የመጨረሻ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

ጨዋነት የጎደለው ባህርይ ማሳየት 

የተሳታፊዎቻችንን እና የደንበኞች ማዕከል ሰራተኞቻችንን ክብር መጠበቅ የሥራችን አንዱ አካል ነው፡፡ ስለሆነም ተሳታፊዎች፡ 

  • ማንኛውንም የማህበረሰባችን አካል እና የደንበኞች ማዕከል ባልደረቦቻችን በጥላቻ፣ በዘር፣ በጎሳ፣ ወይም በማንኛውም መልኩ ማንቋሸሽ፣ መስደብ፣ ክብር ዝቅ ማድረግ፣ ማሾፍ፣ ማስፈራራት፣ መዛት፣ ወይም ደግሞ አካላዊ ጥቃት ማድረስ አይፈቀድም፤ 
  • የ Premise የደንበኞች ማዕከል ቻናሎቻችንን ስህተት ወይም የውሸት በሆኑ ሪፖርቶች ማጨናነቅ፣ የደንበኞች ማዕከል ባልደረቦቻችንን ክብር በጎደለው ሁኔታ ወይም ጥላቻ በሚታይበት ሁኔታ ማነጋገር የለባቸውም፤ 
  • በአፕሊኬሽኑ ውስጥ የቴክኒክ ችግር (“ስህተት”) በሚፈጠርበት ጊዜ፣ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ድርጅታችንን የሚጎዳ ነገር ማድረግ ወይም ደግሞ ለሎች ሰዎች አጋጣሚውን እንዲጠቀሙበት ማበረታታት የለባቸውም፡፡

ትክክለኛነት የጎደለው ባህርይ ማሳየት 

ትክክለኛነት የስራችን ዋና አካል በመሆኑ፣ ተሳታፊዎቻችን የተለያዩ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ማንነታቸውን እንዲደብቁ ወይም ቦታቸውን እንዲያጭበረብሩ አንፈቅድም፡፡ ስለሆነም የ Premise ተሳታፊዎች፡ 

  • ከሞባይል ስልካቸው ውጪ፣ በሌላ በምንም ነገር የ Premise አፕሊኬሽንን መጠቀም ወይም ደግሞ ለመጠቀም መሞከር የለባቸውም፤ 
  • የአፕሊኬሽናችንን አሰራር የሚያበላሹ ሶፍትዌሮችን መስራት፣ ማሰራጨት፣ መጠቀም፣ ወይም ሌሎች ሰዎች እንዲጠቀሙበት ማበረታታት የለባቸውም፤ 
  • አፕሊኬሽናችንን ወይም አገልግሎታችንን ከተለመደው የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ የአጠቃቀም ባህርይ ውጪ በሆነ መልኩ ለመጠቀም መሞከር የለባቸውም፡፡ 

Premise የፕላትፎርሙን አጠቃቀም ደህንነት የማስጠበቅ መብት እና ኃላፊነት ስላለበት፣ የማህበረሰባችንን መመሪያ የሚጥሱ ማንኛውም ተሳታፊዎች ላይ እርምጃ ይወስዳል፡፡ ማለትም መመሪያችንን የሚጥሱ ማንኛውም ተሳታፊዎች አካውንት ይታገዳል፡፡ 

የ Premise ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አካል ስለሆኑ እና በጥናቶቻችን በመሳተፍ ለአጋር ድርጅቶቻችን አጋዥ በመሆንዎ እናመሰግናለን፡፡ የእርስዎ ተሳትፎ ለ Premise ዓላማ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል፡፡