የ Premise የአጠቃቀም ውል
በተግባር ላይ የሚውልበት ቀን: አፕሪል 1፣ 2024
ቀጥሎ የቀረበው የአጠቃቀም ውል (“ስምምነት”) በ Premise ሞባይል አፕሊኬሽን (“አፕ”) አጠቃቀም፣ የ Premise ድረ ገጽ በሆነው “www.premise.com” (“ድረ ገጽ”) አጠቃቀም፣ እንዲሁም በ Premise ፖርታሎች ወይም Premise በሚያቀርባቸው ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎቶች (“ፕላትፎርም”) አጠቃቀም፣ በተጨማሪም በአፑ፣ በድረ ገጻችን፣ ወይም በፕላትፎርሞቻችን (አፑ፣ ድረ ገጹ፣ እንዲሁም ፕላትፎርሞቹ በአንድነት “አገልግሎቶች” ተብለው ይጠራሉ) አማካኝነት በሚያገኟቸው ምርቶች እና አገልግሎቶች አጠቃቀም ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ይህን አገልግሎት ሲጠቀሙ በዚህ ስምምነት ውስጥ የተጠቀሱትን የአጠቃቀም ውሎች፣ በአፕሊኬሽኑ አማካኝነት፣ በድረ ገጻችን፣ ፕላትፎርማችን ወይም በሚቀርቡልዎት የጥናት ተግባራት ውስጥ ያሉትን ህጎች፣ መመሪያዎች፣ እንዲሁም የአሰራር ደንቦች አንድም ሳይቀንሱ ሙሉ በሙሉ እንደተቀበሏቸው ይቆጠራል (ማብራሪያው ወደታች ይገኛል)፡፡ አገልግሎታችንን ከተጠቀሙ ይህን አስገዳጅና ህጋዊ የሆነ ስምምነት አምነው እንደተቀበሉ ይቆጠራል ማለት ነው፡፡ በአፑ ወይም በፕላትፎርማችን አማካኝነት “እስማማለሁ” የሚለውን ቁልፍ ጠቅ በማድረግ ከተጫኑት፣ በዚህ አስገዳጅ እና ህጋዊ የሆነ ስምምነት መስማማትዎን እና ይህን የቀረበውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንደተቀበሉት ይቆጠራል፡፡ ከዚህ በታች እንደተብራራው፣ ይህ ስምምነት እንዳስፈላጊነቱ በየጊዜው ማሻሻያ ወይም ለውጥ ሊደረግበት ይችላል፡፡
እባክዎ ጊዜ ወስደው ይህን ስምምነት እንዲያነቡት እንመክርዎታለን፡፡ በድርጅትዎ ስም የኛን አገልግሎት መጠቀም ከፈለጉ፣ መጠቀም የሚችሉት ድርጅቱ ለእርስዎ በስሙ አገልግሎታችንን እንዲጠቀሙ በፅሁፍ ፍቃድ ከሰጠዎት ብቻ ነው፡፡ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ የሆኑት እርስዎ ወይም በስሙ የኛን አገልግሎት እንዲጠቀሙ የፈቀደልዎት ድርጅት በዚህ የስምምነት ሰነድ ውስጥ “እርስዎ”፣ “የእርስዎ” ወይም “ተጠቃሚ” ተብሎ ይጠራሉ፡፡ ይህን አገልግሎት የሚያቀርበው የ Premise Data Corporation (“PDC”) ነው፡፡ በዚህ የስምምነት ሰነድ ውስጥ ግልጽ ያልሆነልዎት ነገር ካለ እባክዎ በዚህ [email protected] አማካኝነት ወደ PDC የኢሜል መልዕክት በመላክ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ይህ ውል፣ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ በፍርድ ቤት ወይም በክስ ሂደት ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ፣ በግለሰብ ደረጃ ችግሮችን በመነጋገር መፍታትን እንደ አስገዳጅ ሁኔታ መጠቀምን የሚደነግጉ የግልግል ደንቦችን እና የፍርድ ቤት ችሎት ሂደትን የማቋረጥ ደንቦችን ይዟል፡፡
በዚህ ስምምነት ውስጥ የተዘረዘሩትን ሁሉንም ውሎች እና ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ የማይቀበሉ ከሆነ፣ አካውንት አይክፈቱ፣ እንዲሁም አገልግሎታችንን በምንም ዓይነት መልኩ አይጠቀሙ፡፡
የሚፈቀደው እድሜ
ይህን አገልግሎት መጠቀም የሚፈቀደው እድሜያቸው ቢያንስ 18 ለሞላቸው ሰዎች ነው፣ ወይም ደግሞ አገልግሎታችንን ለመጠቀም በማሰብ አካውንት የሚከፈተው ሰው በሚኖርበት ሀገር ውስጥ በእኛ ጥናቶች ተሳታፊ ከሆኑ ከሌሎች አብዛኞች ሰዎች ጋር እድሜው ቢያንስ እኩል መሆን አለበት (ከታች ተብራርቷል)፡፡
ግላዊነት
የ PDC የግላዊነት መመሪያ በድረ ገጽ እና ፕላትፎርማችን ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህ የስምምነት ሰነድ ውስጥም በሚከተለው ሊንክ አማካኝነት ተካቷል (የግላዊነት መመሪያ)፡፡ የግላዊነት መመሪያችን (https://tos.premise.com/privacy-policy/) በአፑ ውስጥ ስላለ መመልከት ይችላሉ፡፡ የግላዊነት መመሪያችንን በደንብ እንዲያነቡት PDC አጥብቆ ያሳስባል፡፡ በዚህ ስምምነት መስማማት፣ በግላዊነት መመሪያችን ጭምር እንደመስማማት ይቆጠራል፡፡
አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚያስፈልጉ ቅድመ-ሁኔታዎች
በዚህ ስምምነት መሰረት በተገለጸው መልኩ አገልግሎታችንን ለመጠቀም እንዲሁም ክፍያ ለማግኘት፣ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ የሆነው ግለሰብ ወይም የግለሰቡ ባለቤት፡
-
- በኩባ፣ ኢራን፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ሱዳን፣ ሶሪያ፣ የዩክሬን/ራሺያ ክሬሚያ ግዛት፣ ወይም ደግሞ በዩ.ኤስ ዲፓርትመንት ኦፍ ትሬዠሪስ ሳንክሽንስ ፕሮግራምስ አማካኝነት ከባድ ማዕቀብ የተጣለበት ሀገር ነዋሪ ወይም ዜጋ መሆን የለበትም (ይህን በተመለከተ መረጃ ከፈለጉ በዚህ ሊንክ ያገኛሉ፡ ማዕቀብ ስለተጣለባቸው ሀገራት መረጃ)፤ ወይም
- በአሜሪካ መንግስት የንግድ ማዕቀብ የተጣለበት መሆን የለበትም፡፡ ይህም በዩ.ኤስ ዲፓርትመንት ኦፍ ትሬዠሪስ ሳንክሽንስ ፕሮግራምስ እና በዩ.ኤስ ዲፓርትመንት ኦፍ ኮሜርስ እና ስቴት አማካኝነት በዩ.ኤስ ኤክስፖርት ሕግጋት አማካኝነት እገዳ የተጣለበት መሆን የለበትም፡፡ እነዚህ እገዳዎች የሚመለከታቸው አካላት ዝርዝር በሚከተለው ሊንክ ውስጥ ይገኛል፡ የኮንሶሊዴትድ ስክሪኒንግ ዝርዝር
PDC ማጭበርበርን መከላከል እና ከህግ ጋር መስማማትን በጣም በትኩረት የሚመለከታቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ ለመመዝገብ እና በጥናቶቻችን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሰዎች በሙሉ (ከታች ተብራርቷል) ህግጋትን አለመጣሳቸውን ለማረጋገጥ እንዲሁም ለደህንነት ሲባል PDC አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ የማጣራት ስራዎችን የማካሄድ ሙሉ ስልጣን እንዳለው ተጠቃሚዎች መስማማት አለባቸው፡፡
በተጨማሪም ተጠቃሚው በሚከተሉት ሀሳቦች መስማማት አለበት፡
-
- ተጠቃሚው በተለያዩ አካላት ማለትም በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት፣ በአሜሪካ መንግስት (በዩ.ኤስ ትሬዠሪ ዲፓርትመንት አማካኝነት እገዳ ከተጣለባቸው የሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ)፣ በአውሮፓ ህብረት እና አባል ሀገራት፣ እንዲሁም ከአሜሪካ ወይም አውሮፓ ህብረት ሀገራት ውጪ የሚኖሩ ከሆኑና በትውልድ ሀገርዎ መንግስት አማካኝነት ማዕቀብ ከተጣለባቸው አካላት ስም ዝርዝር ውስጥ የእርስዎ ስም መገኘት የለበትም፤ እንዲሁም
- ተጠቃሚው ከላይ በተገለጸው ዝርዝር ውስጥ ስማቸው በተካተቱ ሰዎች ወይም አካላት ቁጥጥር የሚደረግበት ወይም አባል የሆነ፣ ወይም በእነዚህ አካላት ስም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤ እንዲሁም
- ተጠቃሚው በአሜሪካ ወይም አውሮፓ ህብረት ህግ እና ደንቦች መሰረት ከ PDC ክፍያ እንዳይከፈለው ወይም አገልግሎቶችን እንዳይሰጥ ማዕቀብ የተጣለበት መሆን የለበትም፤ እንዲሁም
- ተጠቃሚው በየትኛውም የሽብር ተግባር ላይ የተሰማራ ወይም የሽብርተኛ ቡድኖች ጋር ንክኪ ያለው መሆን የለበትም፤ እንዲሁም
- ተጠቃሚው በስቴት ዲፓርትመንት ኤክስኪዩቲቭ ኦርደር 13224 ላይ ስማቸው የተዘረዘሩትን ጨምሮ ከሽብር ጋር ለተገናኙ ሰዎች ወይም አካላት በምንም መልኩ (ገንዘብ ነክ በሆነና ባልሆነ) ድጋፍ የሚያደርግ መሆን የለበትም፤ እንዲሁም
- ተጠቃሚው ለራሱም ይሁን በሌላ ህጋዊ አካል ስም የሚጠቀምም ቢሆን፣ ነገር ግን ቢያንስ 18 ዓመት የሞላው መሆን አለበት (ተጠቃሚው ቢያንስ በሚኖርበት ሀገር በጥናቶቻችን ተሳታፊ የሆኑ አብዛኛው ሰዎች እድሜ ጋር እኩል መሆን አለበት (ከታች ተብራርቷል))፣ እንዲሁም ተጠቃሚው አገልግሎቱን ለመጠቀም በህጋዊ መንገድ የተፈቀደለት እና አገልግሎቱን ሲመርጥም ሆነ ሲጠቀም ሙሉ ሀላፊነት መውሰድ የሚችል መሆን አለበት፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች አንዱንም እንኳን ሳያሟሉ ከቀሩ PDC እርስዎን ተጠያቂ ሊያደርግዎት ይችላል፣ ወይም ደግሞ ወንጀልም ሊሆን ይችላል፡፡ በተጨማሪም ቅድመ ሁኔታዎችን አለማሟላት፣ ይህን በመካከላችን ያለውን ስምምነት ወዲያውኑ እንዲቋረጥ ያደርገዋል፣ በተጨማሪም ጥናቶችን በመስራት ያገኙት የነበረውን ገንዘብ አያገኙም (ከታች ተብራርቷል)፣ እንዲሁም ደግሞ በስምምነቱ መሰረት ጉዳዩን ለሚመለከትወ የህግ ባለስልጣን ልናሳውቅ እንችላለን፡፡
ይህን ውል አክብረው ስምምነቱን ተግባራዊ የሚያደርጉ ተጠቃሚዎች የ PDCን አገልግሎት መጠቀም ይችላሉ – ይህም ማለት ተጠቃሚዎች በሁሉም የ PDC መመሪያዎች መሰረት (በ PDC ድረ ገጽ ላይ የሚለጠፉ፣ በአፑ አማካኝነት የሚተላለፉ፣ እንዲሁም በጥናቶች መመሪያዎች ላይ የሚገለጹትን ያጠቃልላል) አገልግሎቱን ይጠቀማሉ ማለትነው፡፡
ይህን አገልግሎት ለማስተካከል ወይም አፕዴት ለማድረግ አንዳንድ ጊዜ አገልግሎቱ ሊቋረጥ እንደሚችል ተጠቃሚው መረዳት አለበት፡፡ አፕዴት ከተደረገ በኋላ አዳዲስ ፊቸሮችን ተጨምረው ሊያገኙ ይችላሉ፣ ወይም ደግሞ ከዚህ በፊት የነበሩ ፊቸሮችን ላያገኙ ይችላሉ፡፡
ተጠቃሚው አገልግሎቱን ለመጠቀም የራሳቸው መጠቀሚያ መሳሪያ ወይም ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ ዋይፋይ አገልግሎት፣ የመልዕክት አገልግሎት፣ ሞደም፣ ሀርድዌር፣ ሶፍትዌር፣ የቴሌፎን አገልግሎት ሊኖራቸውና ይህንንም በአግባቡ የመጠበቅ ሃላፊነት አለባቸው፡፡ ተጠቃሚው አገልግሎታችንን ለማግኘት የሚጠቀምባቸው መሳሪያዎች በሙሉ የኛን አገልግሎት ለመጠቀም የሚያስችሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡
ተጠቃሚው አገልግሎታችንን ለመጠቀም እና በጥናቶቻችን ለመሳተፍ የሚያወጡትን ወጪዎች ማለትም የኢንተርኔት ወጪ፣ የዋይፋይ ክፍያ፣ የጽሁፍ መልዕክት ክፍያ፣ የዳታ ወይም ሌሎች የገመድ አልባ ቴሌኮም አገልግሎት ወጪ፣ የሶፍትዌር ወይም የመጠቀሚያ መሳሪያ ማዘመኛ ወጪ፣ እና የዳታ ትራንስሚሽን ክፍያዎችን በሙሉ የመሸፈን ሙሉ ኃላፊነት አለበት፡፡
ተጠቃሚው በጥናቶቻችን በሚሳተፉበት ጊዜ (ከታች በተገለፀው መልኩ) መኪና፣ ሞተርሳይክል፣ ስኩተር፣ ወይም ሌላ የግል መጓጓዣዎችን (በአጠቃላይ “ተሽከርካሪዎች” ተብለው ይጠራሉ) የሚጠቀም ከሆነ፣ ተጠቃሚው ተሽከርካሪውን በጥንቃቄ የማሽከርከር እና እንዲሁም ደግሞ በሚነዳበት ጊዜ ስልኩን ወይም ሌላ መጠቀሚያ መሳሪያ መጠቀም የለበትም፡፡ ተጠቃሚው
ተጠቃሚው በጥናቶቻችን በሚሳተፉበት ጊዜ (ከታች በተገለፀው መልኩ) መኪና፣ ሞተርሳይክል፣ ስኩተር፣ ወይም ሌላ የግል መጓጓዣዎችን (በአጠቃላይ “ተሽከርካሪዎች” ተብለው ይጠራሉ) የሚጠቀም ከሆነ፣ ተጠቃሚው ተሽከርካሪውን በጥንቃቄ የማሽከርከር እና እንዲሁም ደግሞ በሚነዳበት ጊዜ ስልኩን ወይም ሌላ መጠቀሚያ መሳሪያ መጠቀም የለበትም፡፡ ተጠቃሚው በአገልግሎት ጊዜ የንብረት መጥፋት ወይም ጉዳት ቢደርስበት፣ ለዚህ ጉዳት ማካካሻ የሚሆን ሕጋዊ ኢንሹራንስ ወይም ዋስትና መግባት ይኖርበታል፡፡ ተጠቃሚው በጥናቶቻችን በሚሳተፍበት ጊዜ ለሚደርሰው የንብረት መጥፋት ወይም አካላዊ ጉዳት PDC ተጠያቂ አለመሆኑን ተጠቃሚው ማወቅ አለበት፤ ከዚህ በታች በተቀመጠው ከተጠያቂነት ነፃ የመሆን በሚገልፀው ክፍል መሰረት፡፡ እንዲሁም በተጠቃሚው ምክኒያት ሌላ ሶስተኛ አካል በሚያነሳው ተጠያቂነት፣ PDC ነፃ መሆኑን ተጠቃሚው መገንዘብ አለበት፡፡
ተግባራት፣ ክፍያ፣ ከአፑ ማውጣት የሚፈቀደው ዝቅተኛ የገንዘብ መጠንና ቀነ ገደብ፣ የሚቆረጥ ገንዘብና ታክስ
አፕሊኬሽናችንን ዳውንሎድ ያደረጉ ተጠቃሚዎች የዳሰሳ ጥናቶችን መስራት፣ ቪዲዮ እና ስክሪንሾቶችን፣ የራሳቸውን ወይም የሚመለከቱትን ሌሎች ነገሮችን ፎቶ እና የተቀረፁ ድምፆችን ማስረከብ፣ ወይም በሌሎች ፕሮጀክቶቻችን (በአጠቃላይ “ተግባር” ተብለው ይጠራሉ) መሳተፍ ይችላሉ፡፡ በእያንዳንዱ ተግባር አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ለምሳሌ የሚሰራው ስራ፣ የሚወስደው ጊዜ፣ ቦታውና የሚሰጠው መልስ (በጥያቄ እና መልስ፣ እንዲሁም ደግሞ በተጠየቀው ቦታ ላይ ያሉ ነገሮችን ፎቶ ወይም ቪዲዮ በማንሳት) በሙሉ በተግባሩ መመሪያ ላይ ይገለጻሉ፣ እንዲሁም በዚህ ስምምነት ውስጥም ተካተዋል፡፡ ከግላዊነት መመሪያ በተጨማሪ፣ የጥናቱ መመሪያ ስለ መረጃ አሰባሰብ፣ አጠቃቀም ወይም ማካፈል ይገልፃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተግባሩ መመሪያ ላይ አንድ ተሳታፊ ጥናቱን በትክክል ሰርቶ ሲያስረክብ፣ ተግባሩ ተገምግሞ ከፀደቀ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚከፈለው ይገልጻል፡፡ ለተግባሩ የተመደበው ክፍያ የሚፈጸመው በዚህ ስምምነት በተገለጸው መሰረት ተግባሩ ተሰርቶ ተቀባይነት ያገኘ እንደሆነ ነው (“ጥናቱ ሲጠናቀቅ” ማለት ነው)፡፡ አካውንት ከፈቱ ወይም ደግሞ ተግባራትን ሰሩ ማለት በድርጅታችን ውስጥ ስራ ተቀጠሩ ማለትን አይደለም፡፡
ማውጣት የሚፈቀደው አነስተኛ የገንዘብ መጠን እና ሂደት፡ ተጠቃሚዎች በአፑ ውስጥ ካቅረብናቸው የክፍያ ማውጫ ዘዴዎች ውስጥ የሚፈልጉትን በመምረጥ የሰሩበትን ገንዘብ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን የክፍያ ሂደት ለማከናወን PDC እንደ Mobile Top-Up፣ PayPal፣ Coinbase እና Payoneer የመሳሰሉ የሶስተኛ ወገን አገልግሎቶችን ይጠቀማል፡፡ በእነዚህ የክፍያ አማራጮች ገንዘብ ለማውጣት፣ ተጠቃሚዎች በአፕሊኬሽኑ ውስጥ ማጠራቀም የሚገባቸው የተለያየ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን አለ፡፡ ይህም ማለት በቂ ጥናቶችን በመሥራት ማውጣት ከሚፈቀደው ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ላይ ካልደረሱ በስተቀር፣ የሰሩበትን ገንዘብ ማውጣት አይችሉም ማለት ነው፡፡ ይህ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን በአፑ ውስጥ የክፍያ አማራጮችን ሲመለከቱ የሚገለጽልዎት ሲሆን፣ መጠኑም እንደየሀገሩ የተለያየ ነው፡፡ ማውጣት የሚፈቀደው ይህ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን በ PDC ወይም ከላይ በጠቀስናቸው የክፍያ ዘዴ አቅራቢ የሆኑ ሶስተኛ አካላት የሚወሰን ነው፡፡ ማውጣት የሚፈቀደው ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ምን ያህል እንደሆነ እና ማሻሻያዎች ተደርገውም ከሆነ ማወቅ እንዲችሉ በየጊዜው ወደ አፑ እየገቡ እንዲፈትሹ እንመክርዎታለን፡፡
ገንዘብ የሚያወጡበት ቀነ-ገደብ፡ ተሳታፊዎች ከአፕሪል 1፣ 2022 ጀምሮ ሰርተው ላጠናቀቁት ተግባር የተከፈላቸውን ክፍያ ተግባሩ ከፀደቀበት አንስቶ እስከ ስድት ወር ውስጥ ገንዘቡን ማውጣት ይኖርባቸዋል (“የገንዘብ ማውጫ ቀነ–ገደብ” ይባላል)፡፡ ከአፕሪል 1፣ 2022 በፊት ሰርተው ያጠናቀቁት ተግባር ከሆነ ደግሞ፣ ገንዘቡን ማውጣት የሚችሉት እስከ ማርች 31፣ 2023 ድረስ ነበር (“የተራዘመ የገንዘብ ማውጫ ቀነ-ገደብ ” ይባላል)፡፡ በተጠቀሱት የገንዘብ ማውጫ ቀነ-ገደቦች ውስጥ የሰሩበትን ገንዘብ ካላወጡ፣ በዚህ ስምምነት በተገለጸው መሰረት የቅጣት ክፍያ ሊጣልብዎት ወይም ደግሞ ገንዘቡን ማውጣት እንዳይችሉ ሊከለከሉ፣ ወይም ደግሞ ሁለቱንም ሊጣልብዎት ይችላል፡፡ ተጠቃሚዎች በአፑ ውስጥ የተጠናቀቁ ተግባራት የሚለው ውስጥ በመግባት፣ ተግባሩን ሰርተው ያስረከቡበትን ቀን እና የተከፈላቸውን የገንዘብ መጠን በመመልከት፣ ያላቸው ባላንስ ምን ያህል ጊዜ እንደሆነው ለማወቅ ይችላሉ፡፡
ገንዘቡን ሳያወጡ ከዘገዩ የሚጣልብዎት የክፍያ ቅጣት፡ ተጠቃሚዎች በአፑ ውስጥ ያላቸውን ገንዘብ ሳያወጡ ከላይ የተገለጸው የገንዘብ ማውጫ ቀነ-ገደብ ካለፈ (“ብዙ ጊዜ የሆናቸው ገንዘቦች”)፣ ለእነዚህ ሳይወጡ ረጂም ጊዜ ላስቆጠሩ ገንዘቦች PDC በየዓመቱ $1 የአሜሪካን ዶላር ቅጣት ሊጥልብዎት ይችላል፡፡
ልዩ የገንዘብ ማውጫ ቀነ-ገደብ፡ ተጠቃሚው አካውንት በከፈተበት ሀገር ከሚፈቀደው ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ላይ በመድረስ ገንዘቡን በጊዜ (በተቀመጠው ቀነ–ገደብ ውስጥ) ለማውጣት የሚያስችል በቂ ጥናቶችን PDC ለተጠቃሚው ካላቀረበ፣ ተጠቃሚው በዚህ አድራሻ አማካኝነት [email protected] ወደ PDC መልዕክት በመላክና ጉዳዩን በማስረዳት ከተቀመጠው የገንዘብ ማውጫ ቀነ–ገደብ/የገንዘብ ቅጣት የእፎይታ ጊዜ እንዲሰጠው መጠየቅ ይችላል፡፡ ከዚያም PDC ጉዳዩን ተመልክቶ አስፈላጊ ከሆነ በራሱ ስልጣን ብቻ (1) ተጠቃሚው ለተወሰነ ጊዜ የክፍያ ቅጣት እንዳይጣልበት ሊያደርግ ይችላል፣ ወይም (2) ተጠቃሚው ማንነቱን የሚያስረዳ በቂ መረጃ ለ PDC ማቅረብ ከቻለ፣ በጥናቱ በተቀመጠው የገንዘብ ዓይነት አማካኝነት በባንክ ወይም ደግሞ PDC ተስማሚ ነው ብሎ ባመነበት ሌላ የክፍያ መንገድ ተጠቃሚው ገንዘቡን እንዲወስድ ሊያመቻች ይችላል፡፡
በክፍያ ዙሪያ PDC የሰራው ስህተት አለ ብሎ ተጠቃሚው ካመነ፣ በዚህ አድራሻ [email protected] አማካኝነት ተጠቃሚው ወደ PDC መልዕክት በመላክ የደንበኞች አገልግሎት ማዕከላችንን ማነጋገር አለበት፡፡
ተጠቃሚው የ PDC ሰራተኛ አይደለም፡፡ ተጠቃሚው በአገልግሎታችን አማካኝነት ከሚያገኘው ገቢ ወይም ተግባራትን በመስራት ከሚያገኘው ገቢ ላይ ተገቢውን ግብር የመክፈል ኃላፊነት አለበት፡፡ PDC እንደ ፎርም 1099 ያሉ የግብር መክፈያ ሰነዶችን በኢሜሪካ ሀገር ውስጥ ለሚኖሩ ተጠቃሚዎቹ መላክ ይችላል፡፡
ማስተካከያዎችን፣ ለውጦችን፣ እንዲሁም ማገድን በተመለከተ
በፈለገው ጊዜ ሁሉ PDC አገልግሎቱን ማሻሻል፣ ማቋረጥ ወይም መተው ይችላል፤ ይህ በአፑ ውስጥ ያሉትን ፊቸሮች፣ ዳታቤዝ እንዲሁም በዳታቤዝ ውስጥ ያሉ ይዘቶችንም ያካትታል፡፡ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ተጠቃሚው አገልግሎታችንን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መጠቀም እንዳይችል፣ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ወይም ተጠያቂነት PDC የማገድ ሙሉ ስልጣን አለው፡፡
PDC ይህን ስምምነት የማሻሻል ሙሉ ስልጣን ያለው ሲሆን፣ ይህ በሚሆንበት ጊዜ በድረገጻችን፣ በፕላትፎርሙ ወይም በአፑ ውስጥ፣ ወይም በኢሜል እና በፖስታ አማካኝነት የተደረገውን ለውጥ ተጠቃሚዎች እንዲያውቁት መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ ተጠቃሚዎች የተደረገውን ለውጥ የማንበብና የማወቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ለውጡ ከተደረገ በኋላ ተጠቃሚዎች በአገልግሎታችን መጠቀም ከቀጠሉ፣ በስምምነቱ ውስጥ የተጠቀሱትን ውሎች እና ቅድመ ሁኔታዎች እንደተቀበሉት ይቆጠራል፡፡
በአፑ፣ በድረ ገጽ፣ እና በፕላትፎርማችን ላይ ያሉ ንብረቶች እና የአዕምሯዊ ንብረት መብት
በአገልግሎታችን ወይም በአፑ፣ በድረ ገጻችን፣ እና በፕላትፎርማችን ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ንብረቶች ማለትም የንግድ ምልክቶች፣ ጽሁፍ፣ ግራፍና ግራፊክስ ምስሎች፣ ዳታዎች፣ መለኪያዎች፣ ሎጎዎች፣ የበተን ምስሎች፣ ፎቶዎች፣ የድምጽ ክሊፖች፣ ዳውንሎድ የሚደረጉ ፋይሎች፣ የተጠናቀሩ መረጃዎች፣ ሶፍትዌር እና ማቴሪያሎች፣ እንዲሁም ሌሎች (በአንድነት “ንብረቶች”) በቅጂ መብት፣ በንግድ ምልክት፣ በአገልግሎት ምልክቶች፣ በፓተንት፣ በንግድ ሚስጢሮች፣ እንዲሁም በግል ንብረት መብትና ህግጋቶች ጥበቃ የሚደረግላቸው የ PDC የተመዘገቡ አዕምሯዊ ንብረቶች መሆናቸውን ተጠቃሚው ይስማማል፡፡ በ PDC የተጻፈ ፍቃድ እስካላገኘ ድረስ፣ ማንኛውም የአገልግሎታችን ተጠቃሚ የሆነ ሰው፣ እነዚህን የአዕምሮ ንብረቶች መሸጥ፣ ለሌላ ሰው ፍቃድ መስጠት፣ ማከራየት፣ መለወጥ፣ ማሰራጨት፣ መኮረጅ፣ አስመስሎ መስራት፣ ማስተላለፍ፣ ትዕይንተ ህዝብ ላይ መጠቀም፣ ማተም፣ ማሻሻል፣ ማስተካከል፣ ወይም አቀናብሮ ማቅረብ አይችልም፤ እንዲሁም ሌሎችን ሰዎች ወደ PDC እና አገልግሎቶቹ ወይም ምርቶቹ ለመጋበዝ ካልሆነ በስተቀር፣ ተጠቃሚው የ PDCን የንግድ ምልክቶች መጠቀም አይችልም፡፡ የተገለጹትን የቅጂ መብቶች እና ተዛማች የንብረት ባለቤትነት መብቶችን እስካልጣሰና ለንግድ ዓላማ እስካልተጠቀመባቸው ድረስ፣ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ የሆነ ሰው የተወሰኑትን ንብረቶች ከአፕሊኬሽናችን፣ ከድረ ገጻችን፣ ወይም ከፕላትፎርማችን ላይ ዳውንሎድ ወይም ፕሪንት በማድረግ መገልገል ይችላል፡፡ ከ PDC የጽሁፍ ፍቃድ ሳይኖረው፣ ማንኛውንም በአፕሊኬሽናችን፣ በድረ ገጻችን፣ ወይም በፕላትፎርማችን ላይ የሚገኙ ንብረቶችን፣ ማቴሪያሎችን እና ዲዛይኖችን ለሌላ ያልተፈቀደ ዓላማ ለማዋል አስመስሎ መስራት፣ መኮረጅ ወይም ማሰራጨት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
በዚህ ስምምነት ውስጥ በግልጽ ላልተቀመጡ ዓላማዎች የእኛን ንብረቶች መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ በግልጽ ያልተቀመጠ ከሆነ፣ ይህን መብት ያለን እኛ ብቻ ነን ማለት ነው፡፡
በማያሻማ ሁኔታ እስካልተገለፀ ድረስ፣ የዚህ አገልግሎት የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤት PDC (እና እንደአግባብነቱ ደግሞ የባለቤትነት ፈቃድ ሰጪዎች) ብቻ ነው፡፡ በአፑ፣ በድረገጽ፣ እና በፕላትፎርማችን ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ንብረቶች ባለቤት PDC ወይም የንብረት አቅራቢ አካላት ነው፡፡ በአፑ፣ በድረ ገጹ እና በፕላትፎርሙ ላይ የሚገኙ ጥንቅሮች ወይም ንብረቶች ሙሉ በሙሉ የ PDC ንብረት ናቸው፡፡
ይህ ስምምነት እንደ ሽያጭ አይቆጠርም፣ በመሆኑም የትኛውንም ዓይነት የድርጅታችንን የአገልግሎት ባለቤትነት መብት፣ የንብረት ወይም የአዕምሯዊ ንብረት መብትን እንዲጠቀሙበት የሚፈቅድ ሰነድ አይደለም፡፡
ተጠቃሚው የሚያበረክታቸው
አገልግሎታችንን የሚጠቀም ማንኛውም ተጠቃሚ በአፑ፣ በድረ ገጻችን፣ ወይም በፕላትፎርማችን ወይም በጥናቶቻችን አማካኝነት የሚያበረክታቸውን ተግባራት (“ተጠቃሚው የሚያበረክታቸው”)፣ PDC ያለምንም ገደብ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ ሊገደብ በማይችል መልኩ፣ ያልምንም የሮያሊቲ ክፍያ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱም ተጠቃሚው ያበረከታቸውን ነገሮች ለማንኛውም ዓላማ ሌላ አካል (የጥናት ተግባራትን እንዲያከናውንለት ለ PDC ስራ የሰጠ ማንኛውም አካል) እንዲጠቀምበት ፍቃድ መስጠት የሚያስችለው ሙሉ መብት PDC አለው፡፡ ተጠቃሚው በሚያበረክታቸው ተግባራት ላይ ምንም ዓይነት የሞራል መብት ወይም ደግሞ የአበርካቹ ስም እንዲጠቀስለት የመጠየቅ መብት አይኖረውም፡፡ PDC ተጠቃሚው የሚያበረክታቸውን ማንኛውንም ዓይነት ተግባራት ከአፑ፣ ከድረ ገጹ፣ ወይም ከፕላትፎርሙ ላይ ምክኒያታዊ በሆነ ሁኔታ የማስወገድ (ለምሳሌ ሌሎች ሶስተኛ አካላት ወይም ባለስልጣን የሆነ አካል፣ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ የሆነው ሰው በላከልን ተግባራት ላይ ቅሬታ ቢያነሳ)፣ ወይም ያለምንም ምክኒያት ተጠቃሚው ያበረከተውን ተግባራት አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ የማስወገድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአገልግሎታችን ተጠቃሚ የሆነ ሰው የሚከተሉትን ነገሮች ያረጋግጣል (i) ተጠቃሚው በተግባራቶቻችን ላይ በመሳተፍ የተለያዩ አስተዋጾዎችን ለ PDC እና ለአፑ፣ ለድረ ገጹ፣ እና ፕላትፎርሞቹ የማበርከት መብት እና ስልጣን ያለው መሆኑን እና፣ ከዚያም ቀጥሎ ያበረከታቸውን ተግባራት እኛ እንድንጠቀምበት መብቱን አሳልፎ የሰጠን መሆኑን፤ (ii) ተጠቃሚው የሚያበረክታቸው ተግባራት የማንኛውንም ሶስተኛ አካል መብት ወይም የአዕምሯዊ ንብረት የሚጥስ እና PDCን፣ ሰራተኞቹን፣ ኮንትራክተሮቹን፣ ኦፊሰሮቹን፣ ዳይሬክተሮቹን፣ ወኪሎቹን፣ ወይም PDCን ጥናት እንዲያከናውንለት ስራ የሰጠውን ሶስተኛ አካላት ተጠያቂ የሚያደርግ መሆን የለበትም፤ (iii) ተጠቃሚው የሚያበረክታቸው እና ተግባራትን በሚሰራበት ወቅት፣ ተጠቃሚው ማክበር የሚገባውን ሌላ ሶስተኛ አካል ያወጣውን ህግ እና ደንብ የሚጥስ መሆን የለበትም፤ (iv) ተጠቃሚው የሚያበረክታቸው ማንኛውም አይነት ተግባራት ምንም ዓይነት ህግጋትን እና ደንቦችን የሚጥሱ መሆን የለባቸውም፡፡
ከላይ በተገለፀው የግላዊነት መመሪያ መሰረት፣ ተጠቃሚው የሚያስረክበን ማንኛውም ነገሮች የግል መረጃዎችን የሚይዝ ከሆነ፣ የግላዊነት መመሪያችን በሚያዘው መሰረት PDC የግል መረጃውን ጥበቃ ያደርጋል፡፡
ተጠቃሚው በሚያስረክቡን ተግባራቶች ውስጥ የተጠቃሚው የግል መረጃ ካለ በሚከተለው መልኩ አገልግሎት ላይ እንዲውል ፍቃድ ይሰጣል፡ ሀ) በዚህ ስምምነት ለተቀመጡት ዓላማዎች PDC እንዲጠቀምበት ፈቅዷል፤ ለ) PDC ለደንበኞቹ እንዲጠቀሙበት መረጃውን ማካፈል (ደንበኞችም ለእነርሱ ሌሎች ደንበኞች ማካፈል እና በሶሻል ሚዲያ ገፆች እና በሌሎች ፕላትፎርሞች ላይ ፖስት ማድረግ እንዲችሉ) ፈቅዷል፡፡ በዚህ ስምምነት ከተስማሙ፣ በዚህ ፅሁፍ በተገለፀው መልኩ የተጠቃሚውን የግል መረጃ አገልግሎት ላይ ማዋል እንድንችል ፍቃድ ሰጥተውናል ማለት ነው፡፡
አስተያየት
አገልግሎታችንን የሚጠቀም ማንኛውም ተጠቃሚ በአፑ፣ በድረ ገጻችን፣ ወይም በፕላትፎርማችን ወይም በጥናቶቻችን አማካኝነት የሚያጋሩንን አስተያየቶችን፣ ሃሳቦችን፣ የማሻሻያ ጥያቄዎች፣ ምክሮች ወይም የአዕምሯዊ ንብረት መብትን ጨምሮ ተጠቃሚው አልያም ከአገልግሎቱ ጋር በተያያዘ ሌላ ሶስተኛ አካል የሚሰጠንን መረጃ (በአንድላይ “አስተያየት” ይባላሉ)፣ PDC ያለምንም ገደብ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ ሊገደብ በማይችል መልኩ፣ ያልምንም የሮያሊቲ ክፍያ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱም ተጠቃሚው ያበረከታቸውን አስተያየቶች ለማንኛውም ጥቅም ሌላ አካል (የጥናት ተግባራትን እንዲያከናውንለት ለ PDC ስራ የሰጠ ማንኛውም አካል) እንዲጠቀምበት ፍቃድ መስጠት የሚያስችለው ሙሉ መብት PDC አለው፡፡
የሚሰጡን ማንኛውም አስተያየት የሌላ የሶስተኛ ወገንን መብቶች ማለትም የቅጂ መብት፣ የንግድ ምልክት፣ ግላዊነት ወይም ሌሎች መብቶችን የሚጥስ መሆን የለበትም፡፡
አርቴፊሺያል ኢንተሊጀንስ እና የመረጃ ትንተና
በግላዊነት መመሪያችን በተገለጸው መሰረት PDC በራሱ እና ከተጠቃሚዎች የሚሰበስባቸውን መረጃዎች ማለትም ምስሎች፣ ቪዲዮዎች፣ የድምፅ ቅጂዎች፣ ስክሪንሾት እና ፎቶዎች፣ የአርቴፊሺያል ኢንተሊጀንስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሊተነትን ይችላል፡፡ የ PDC ደንበኞችም PDC የሚሰጣቸውን መረጃዎች የአርቴፊሺያል ኢንተሊጀንስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም መተንተን ይችላሉ፡፡
ችግር ሲያጋጥም፣ ለደህንነት ቅድሚያ መስጠት፣ እና ችግርን መከላከል
ተሳታፊያችን ጥናቶችን በሚያከናውንበት ጊዜ ችግር ካጋጠመው፣ PDC በራሱ ስልጣን እና በራሱ ውሳኔ ላይ ብቻ መሰረት አድርጎ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ የሆነውን ሰው ሊያግዝ ይችላል፡፡ ተጠቃሚው ችግር ካጋጠመው ስንል፣ አዲስ ስልክ የሚያስፈልግ ከሆነ፣ የጠፋ ወይም የተበላሸ ስልክ መተካት የሚያስፈልግ ከሆነ፣ ወይም ደግሞ አካላዊ ጉዳት ደርሶበት፣ የግል ንብረቱ ወድሞበት፣ ከስራ ታግዶ፣ ወይም ቅጣት ተቀጥቶ ከሆነ ለማለት ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ እገዛ እንዲደረግልዎት ለመጠየቅ በዚህ አድራሻ [email protected] ለ PDC ኢሜል ይጻፉ፡፡
የግል ደህንነትን መጠበቅ እና ህግን ማክበር PDC ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ምንጊዜም ቢሆን የአገልግሎታችን ተጠቃሚዎች ለደህንነታቸው ቅድሚያ ሰጥተው እንዲሁም ለራሳቸው እና በአካባቢያቸው ላሉ ሌሎች ሰዎችም ኃላፊነት በሚሰማው መልኩ፣ ራሳቸውን ወይም ሌላ ሶስተኛ ወገንን ለአካላዊ ጥቃት፣ ንብረት መውደም በማያጋልጥ መልኩ በጥናቶቻችን መሳተፍ ይገባቸዋል፡፡ ለአካላዊ ጉዳት፣ የግላዊ መብት መጣስ፣ ወይም ለንብረት መውደም የሚያጋልጡ ማንኛውንም ዓይነት እንቅስቃሴዎች PDC አያበረታታም ወይም አይደግፍም፡፡ ተጠቃሚዎቻችን ሁልጊዜ ህግን ማክበር፣ አለመጣስ፣ ራሳቸውን እና በዙሪያቸው ያሉ ሌሎች ሰዎችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ምንም ዓይነት ህገ ወጥ የሆኑ ተግባራትን ማከናወን የለባቸውም፡፡ ተጠቃሚው ያለ ጥንቃቄ ማሽከርከር፣ ስልክ ወይም ደግሞ ሌሎች የኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎችን በሚጠቀሚበት ጊዜ ተሽከርካሪዎችን ማሽከርከር የለባቸውም፡፡
የሚከለከሉ ነገሮች
ተጠቃሚው አገልግሎታችንን ወይም ንብረቶቻችንን ክልክል ለሆኑ ዓላማዎች ወይም በዚህ ስምምነት ውስጥ ለተከለከሉ ዓላማዎች፣ ወይም የ PDCን እና የሌሎችን መብት በሚጥስ መልኩ መጠቀም የለበትም፡፡
በመሆኑም ተጠቃሚው የሚከተሉትን ነገሮች ላለማድረግ መስማማት አለበት፡
-
- ለተጠቃሚዎች የማይፈቀዱ የአገልግሎት ክፍሎችን ወይም የ PDCን የኮምፒውተር ሲስተም በምንም መልኩ ይሁን መጠቀም አሊያም ደግሞ ሲስተሙ ላይ ችግር መፍጠር የለበትም፤
- የ PDCን ኮምፒውተር ሲስተም ወይም ኔትወርክ ማጥቃት፣ ሲስተሙ ላይ ክፍተቶች መኖር አለመኖራቸውን ለማወቅ መሞከር ወይም መፈተሽ፣ ወይም ምንም ዓይነት የኮምፒውተር ሲስተማችንን ደህንነት መጣስ የለበትም፤
- PDC የአገልግሎቱን ወይም የንብረቱን ደህንነት ለመጠበቅ ያስቀመጣቸውን የቴክኖሎጂ ዘዴዎች ለመጣስ መሞከር የለበትም፤
- የኛን ሶፍትዌሮች ወይም አፕሊኬሽን ኮዶች ዲኮምፓይል፣ ዲስአሴምብል ማድረግ፣ ወይም በሪቨርስ ኢንጅነሪንግ ዘዴዎች መቀየር ወይም መለወጥ የለበትም፤
- በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ ወይም በሚኖሩበት ሃገር፣ ክልል፣ እና አካባቢ ተፈጻሚነት ያላቸውን ህጎች እና ደንቦች መጣስ የለበትም፤
- የሰዎችን ግላዊነት መጣስ የለበትም፤
- ለሰዎች ክፍት ባልሆነ ቦታ፣ ወይም ሰዎች ብቻቸውን ለመሆን በማሰብ በሚሄዱበት ቦታ የእኛን አገልግሎት መጠቀም የለበትም፤
- ከላይ የተዘረዘሩትን ክልከላዎች ሌላ ሰው እንዲያደርጋቸው መገፋፋት የለበትም፡፡
ምዝገባና ደህንነት
ተጠቃሚው በእኛ ጥናቶች ወይም ተግባራት ውስጥ ለመሳተፍ ወይም ጥናቶቻችንን ለመመልከት ከፈለገ፣ አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ማድረግ፣ አካውንት መፍጠር፣ የትውልድ ዘመን መረጃ ማስገባት፣ እና እንደ የቦታ ማግኛ የመሳሰሉ አንዳንድ የስማርት ስልክ ፍቃዶችን መፍቀድ ይኖርበታል፡፡ ተጠቃሚው እንደሚኖርበት ቦታ የሚለያይ ቢሆንም፣ ነገር ግን ተጠቃሚው (i) የሚጠቀምበትን የ Google ወይም Apple ኢሜል እንዲያስገባ፣ ወይም (ii) የ PDCን አገልግሎት ለመጠቀም በመመዝገብ የፓስወርድና የተጠቃሚ ስም (“የ PDC ተጠቃሚ መለያ” በመባል ይታወቃል) እንዲፈጥር ይጠየቃል፡፡
ተጠቃሚው ፕላትፎርማችንን ለመጠቀም፣ አካውንት እንዲከፍት፣ ስም፣ የትውልድ ዘመን፣ የመኖሪያ አድራሻ፣ እና ተጠቃሚውን የምናነጋግርበት የመገናኛ መረጃ (ስልክ ቁጥር እና ኢሜል)፣ ፓስወርድና የ PDC ተጠቃሚ መለያ እንዲፈጥር ይጠየቃል፡፡
የአገልግሎታችን ተጠቃሚ በምዝገባ ወቅት ለ PDC ትክክለኛ፣ የተሟላ፣ እና የቅርብ ጊዜ መረጃዎችን ለ PDC መስጠት ይኖርበታል፡፡ ተጠቃሚው ይህን ካላደረገ ይህን ስምምነት እንደጣሰ ስለሚቆጠር ወዲያውኑ አካውንቱ ይታገዳል፡፡
ተጠቃሚው (i) የሌላ የ PDC አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነን ሰው መለያ ስም ሆን ብሎ መጠቀም የለበትም፤ (ii) የሌላ ሰው መብት የሆነን የመጠሪያ ስም ያለምንም ፍቃድ እንደራስ መለያ በመጠቀም የ PDCን መአገልግሎት መጠቀም የለበትም፤ (iii) ሌላ ሰው የሚጠቀምበትን ኢሜል መጠቀም የለበትም፡፡ ተጠቃሚዎች የ PDC አገልግሎትን ለመጠቀም የአገልግሎት መለያ ስም እንዳይፈጥሩ ወይም መመዝገብ እንዳይችሉ የመከልከል ሙሉ ስልጣን ያለው PDC ብቻ ነው፡፡
ተጠቃሚው የ PDC አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚጠቀምባቸውን ፓስወርድ እና ሌሎች ተጨማሪ የአካውንት መረጃዎችን ሚስጢራዊነት የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት፡፡
የ PDCን አገልግሎት ወይም አፕልኬሽናችንን ለመጠቀም ከአሜሪካ ሀገር ውጭ በሆነ በሌላ ሀገር ተመዝግቦ፣ ነገር ግን አገልግሎቱን በአሜሪካ ሃገር ውስጥ ሆኖ መጠቀም አይፈቀድለትም፡፡
ካሳ
በአገልግሎታችን የሚጠቀም ሰው ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ለሚያደርጋቸው ማንኛውም ተግባራት ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡ በ PDC ጥፋት ወይም ቸልተኝነት የተፈጠረ ሊባል ከሚችል ጥፋት ውጪ፣ ተጠቃሚው (i) አገልግሎታችንን ሲጠቀም ወይም ያላግባብ ሲጠቀም በሚፈጠር፤ (ii) የአገልግሎታችንን አካል የሆነ የትኛውንም ነገር ሲጠቀም በሚፈጠር፤ ወይም (iii) ይህንን ስምምነት በመጣስ በሚፈጠር ማንኛውም ችግር ህግ በሚፈቅደው መሰረት ተጠቃሚው ራሱን መከላከል፣ ራሱን በራሱ መካስ ይኖርበታል፤ እንዲሁም ተጠቃሚው PDCን ወይም አጋር ድርጅቶችን እና የአጋር ድርጅቶችን ሰራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ አቅራቢዎች፣ እና ተወካዮች ከሁሉም ዓይነት ተጠያቂነት፣ ይገባኛል ጥያቄ፣ የጠበቃን ጨምሮ ከማንኛውም ዓይነት ወጪዎች ተጠያቂ ማድረግ የለበትም፡፡
ዋስትና አለመስጠትን
በሕግ ጥያቄ መሰረት ካልሆነ በስተቀር፣ ድርጅታችን የሚያቀርበውን አገልግሎት (አፑን፣ ድረ ገጹን፣ ፕላትፎርሙን እና ማንኛውንም ዓይነት ሶፍትዌር ጨምሮ) ለተጠቃሚዎቹ ያቀረበው “አሁን ባለበት ሁኔታ” በሚል መርህ ላይ ተመስርቶ ሲሆን፣ ነገር ግን ለንግድ ዓላማ በብቃት ስለማገልገሉ፣ ወይም የማንኛውንም ፍላጎት ግብ በብቃት የሚያሳካ ስለመሆ፣ ወይም የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነትን መብት የማይጥስ ስለመሆኑ ምንም ዓይነት ዋስትና አይሰጥም፡፡ (1ኛ) አገልግሎቱ ከቫይረስ ወይም ከሌላ ጎጂ ነገሮች ነፃ ስለመሆኑ፣ (2ኛ) አገልግሎቱ በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም ቦታ ላይ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ሁልጊዜ አገልግሎት የሚሰጥ ስለመሆኑ፣ (3ኛ) የሚከሰቱ እንከኖች ወይም ችግሮች የሚስተካከሉ ስለመሆኑ፣ (4ኛ) አገልግሎቱን መጠቀም የተጠቃሚውን ፍላጎት የሚያሟላ ስለመሆኑ PDC ምንም ዓይነት ዋስትና አይሰጥም፡፡ በተለይ ደግሞ፣ በአገልግሎቱ አማካኝነት ስለሚቀርቡት መረጃዎች ትክክለኛነት ምንም ዓይነት ዋስትና አይሰጥም፡፡ ተጠቃሚዎች የኛን አገልግሎት መጠቀም ያለባቸው ለሚከሰቱ ማንኛውም ነገሮች ራሳቸው ሙሉ ኃላፊነቱን ወስደው ነው፡፡
የአንዳንድ ሀገራቶች ሕግ፣ በዋስትና ላይ የሚጣሉ ገደቦችን ወይም ሊደርሱ ለሚችሉ አንዳንድ ጉዳቶች ኃላፊነት አለመውሰድን ይከለክላሉ፡፡ በእርስዎ ሀገር ውስጥ እንዲህ ዓይነት ህግ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ፣ ከላይ የተዘረዘሩት የዋስትና ገደቦች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በእርስዎ ላይ ተፈጻሚ ላይሆኑ ስለሚችሉ ተጨማሪ ሌሎች መብቶች ሊኖሩዎት ይችላሉ ማለት ነው፡፡
የተጠያቂነት ገደብ
በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን የ PDC ኦፊሰሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ባለቤቶች፣ ሰራተኞች፣ ኤጀንቶች፣፣ ሻጮችም ሆኑ አቅራቢዎች፣ በአገልግሎቱ (ወይም በአገልግሎቱ አማካኝነት በሚቀርቡ መረጃዎች ጋር በተያያዘ) ለሚከሰቱ ማንኛውም፡ (1ኛ) የገንዘብ ኪሳራዎች ወይም በልዩ ምክኒያት፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ፣ ወይም በቅጣት መልኩ ለሚመጡ ተገማች የሆኑ ጉዳቶችና ኪሳራዎች በሙሉ ተጠያቂ አይደሉም፣ (2ኛ) የኮምፒውተር ወይም የአፕሊኬሽን እክሎች፣ ቫይረሶች፣ ትሮጃን ቫይረሶች፣ ወይም ተመሳሳይ ችግሮች ተጠያቂ አይደሉም (ምንጫቸው ከየትም ቢሆንም እንኳን)፣ (3ኛ) በመረጃዎች ላይ ሊኖሩ በሚችሉ ስህተቶች እና ጉድለቶች፣ ወይም ፖስት ባደረግናቸው፣ በኢሜል በላክናቸው፣ ወይም በአገልግሎቱ አማካኝነት በሚያገኟቸው መረጃዎች ምክኒያት ሊከሰቱ ከሚችሉ ኪሳራዎች ወይም ጉዳቶች በሙሉ ተጠያቂ አይደሉም፣ (4ኛ) ከ 100 ዶላር በላይ ለሆነ ኪሳራ በሙሉ ተጠያቂ አይደሉም (ተጠቃሚው ለአገልግሎቱ ክፍያ ፈጽሞ ከሆነና፣ ይህ የተፈጸመው ገንዘብ ከ 100 ዶላር በሚበልጥበት ጊዜ የተጠያቂነት መጠኑ በተከፈለው ገንዘብ መጠን ልክ እንዲሆን ይደረጋል)፡፡ በተጨማሪም ተጠቃሚው አገልግሎታችንን መጠቀም ፈልጎ ነገር ግን ሳይችል ሲቀር፣ ወይም ደግሞ አገልግሎታችንን በሚጠቀምበት ጊዜ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ለሚያጋጥመው ኪሳራ ወይም ተጠያቂነት PDC ተጠያቂ አይደለም (ማለትም የሚጠቀምበት ስልክ ወይም ኮምፒውተር ቢበላሽ፣ አገልግሎታችንን እንዳይጠቀም በኢንተርኔት ሰርሳሪዎች ስልኩ ቢቆለፍ፣ ተግባራትን ሰርቶ በሚያስረክብበት ጊዜ በሚፈጠር መስተጓጎል፣ ወይም በኢንተርኔት ወይም ቴሌኮም አገልግሎት መቋረጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን ያካትታል)፡፡
የአንዳንድ ሀገራቶች ሕግ፣ ሊደርሱ በሚችሉ አንዳንድ ጉዳቶች ላይ ኃላፊነት አለመውሰድን ይከለክላሉ፡፡ በእርስዎ ሀገር ውስጥ እንዲህ ዓይነት ህግ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ፣ ከላይ የተዘረዘሩት ገደቦች በእርስዎ ላይ ተፈጻሚ አይሆኑም፡፡ ላይሆኑ ስለሚችሉ ተጨማሪ ሌሎች መብቶች ሊኖሩዎት ይችላሉ ማለት ነው፡፡ በደንብ ግልፅ እንዲሆንልዎት ከላይ የተዘረዘሩት ገደቦች በኒውጀርሲ በሚኖሩ ተሳታፊዎቻችን ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
አገልግሎት ማቋረጥ
በምክኒያትም ይሁን ያለምክኒያት፣ PDC አስፈላጊ ሆኖ ብሎ ባመነበት ሰዓት ላይ ተጠቃሚው አገልግሎታችንን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ መጠቀም እንዳይችል አካውንቱን ማገድ ይችላል (በተለይ ተጠቃሚው በ PDC ላይ ጥሰት የፈፀመ ሆኖ ከተገኘ፣ PDC ያለምንም ማስጠንቀቂያ ተጠቃሚው አገልግሎቱን ማግኘት እንዳይችል ማገድ ይችላል)፡፡
ተጠቃሚው በማንኛውም ሰዓት ላይ የ PDCን አገልግሎት መጠቀም ማቆም ከፈለገ፣ አፑ ውስጥ አካውንት የሚለው ክፍል ውስጥ በመግባት መለያውን መዝጋት፣ አፕሊኬሽኑን ከስልክ ላይ በማጥፋት፣ እንዲሁም በዚህ ኢሜል [email protected] አማካኝነት ወደ PDC በመጻፍ አካውንቱ ከሲስተማችን ላይ እንዲጠፋለት መጠየቅ ይችላል፡፡
ተጠቃሚው አገልግሎታችንን ላለመጠቀም ወስኖ አካውንቱ ከሲስተማችን ላይ እንዲጠፋ ካስደረገ በኋላ፣ በሌላ ግዜ ድጋሚ አገልግሎታችንን መልሶ መጠቀም አይችልም፡፡
አገልግሎቱ ከተቋረጠ በኋላ፣ በዚህ ስምምነት ውስጥ ከተዘረዘሩት ደንቦች ውስጥ ተፈጻሚነታቸው የሚቀጥሉ ደንቦች በሙሉ ማለትም የክርክር ወይም ግጭት አፈታት ምርጫ ደንብ፣ ተሳታፊው ያበረከታቸው አስተዋጾዎችን የሚመለከቱ የባለቤትነትን መብት የሚጠቅሱ ደንቦች፣ የተገደበ ኃላፊነትን የሚጠቅሱ ደንቦች፣ እንዲሁም ዋስትና ያለመስጠትን የሚጠቅሱ ደንቦች በሙሉ ተፈጻሚነታቸው የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የግጭት አፈታት፣ የፍርድ ሂደትና የህግ ምርጫ
ይህ ስምምነት ተፈጻሚ የሚሆነው በካሊፎርኒያ ግዛት ሕግ መሰረት ሲሆን፣ ስምምነቱም ልክ ሁለት በካሊፎርኒያ ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደሚፈጽሙት ተደርጎ ይተገበራል፡፡
በድርጅታችን እና በተጠቃሚው መካከል ውዝግብ ከተነሳ፣ ሁለቱ አካላት ጉዳያቸውን በሳንፍራንሲስኮ ካሊፎርኒያ ግዛት በሚገኝ ፍርድ ቤት ለማካሄድ ይስማማሉ፡፡ ሁለቱ አካላት ጉዳያቸውን በግልግል መፍታት ካልቻሉ ውዝግቡን በፍርድ ቤት ለመፍታት የተስማሙ መሆኑ እንዳለ ሆኖ፣ የፍርድ ሂደቱም የሚከናወነው በዩኤስኤ ሳንፍራንሲስኮ ካሊፎርኒያ በሚገኘው የስቴት እና ፌዴራል ፍርድ ቤት እንደሚሆን ይስማማሉ፤ ወይም የፌዴራል ፍርድ ቤቱ ኬዙን ከኖርዘርን ዲስትሪክት ኦፍ ካሊፎርኒያ የሳንፍራንሲስኮ ዲቪዥን የተለየ ወደሆነ ሌላ ፍርድ ቤት ከመራው በዚያው ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
በዚህ ስምምነት በግልፅ ሁኔታ የተቀመጠው እንዳለ ሆኖ፣ ከዚህ ስምምነት፣ ከአፑ፣ ከድረ ገጹ፣ ከፕላትፎርም ወይም አገልግሎታችን፣ ወይም ከተያያዥ ማስታወቂያዎቻችን ጋር በተያያዘ የሚነሳ አለመግባባት ወይም ጭቅጭቅ የግልግል ሂደቱ በሚጀመርበት ጊዜ ተፈጻሚነት ባለው የ JAMS, Inc. (“JAMS”) የዳኝነት ህግ እና ደንቦች መሰረት የሚፈታ ይሆናል፡፡ በግልግል የፍርድ ሂደቱ ውስጥ የማይካተቱት ከአዕምሯዊ ንብረት፣ የእርስዎ፣ የ PDC ወይም ለ PDC ፍቃድ የሰጠው አካል የንግድ ሚስጢሮች፣ የቅጂ መብቶች፣ የንግድ ምልክቶች፣ እንዲሁም የባለቤትነት መብቶች ጋር የተያያዙ ጥሰቶች ብቻ ናቸው፡፡
ይህ ስምምነት ቢቋረጥም እንኳን፣ ሊነሱ የሚችሉ ውዝግቦችን በግልግል የመፍታት ስምምነቱ አይቋረጥም፡፡ የዳኝነት ሂደቱ የሚከናወነው ከአንድ የግልግል ዳኛ ፊት በመቅረብ ይሆናል፡፡ ከዚህ ስምምነት ጋር በተያያዘ በሚነሳ ማንኛውም የግልግል ሂደት ውስጥ፣ የግልግል ሂደቱን የሚመራው ዳኛ ከዚህ ስምምነት ተቃራኒ በሆነ መልኩ ለከሳሹ ሊፈርድለት አይገባም፡፡ የግልግል ሂደቱን የሚመራው ዳኛ በሁለቱ ማለትም በከሳሽ እና ተከሳሽ ስምምነት የሚመረጥ ይሆናል፡፡ ከሳሹ ላነሳው የይገባኛል ጥያቄ ፍርድ እንዲሰጠው ለመጠየቅ የግልግል ዳኝነት ሂደት እንዲጀምሩ ተከሳሹን አካል በፅሁፍ ካሳወቀው በሠላሳ (30) ቀናት ውስጥ ሁለቱ ወገኖች የግልግል ሂደቱን ለመምራት በሚሰየመው ዳኛ ማንነት ላይ መስማማት ካልቻሉ፣ በህገ መመሪያው መሰረት JAMS የፍርድ ሂደቱን የሚመራውን ገላጋይ ዳኛ የሚሰይም ይሆናል፡፡ የተሰየመው ዳኛ የወሰነው በፅሁፍ የተገለፀ ውሳኔ፣ የመጨረሻ ውሳኔ ሆኖ ሁለቱንም ወገኖች የሚያስማማ እና በየትኛውም ፍርድ ቤት ላይ ተፈጻሚነት ያለው ነው፡፡ የፍርድ ሂደቱ የሚጀምረው እና የሚከናወነው በእንግሊዝኛ ቋንቋ አማካኝነት በሳንፍራንሲስኮ ካሊፎርኒያ ሲሆን፣ ሁለቱ ወገኖች ከተስማሙ የፍርድ ሂደቱን በኦንላይን ማድረግ ይችላሉ፡፡ በዚህ ስምምነት የተገለፀው የግልግል ዳኝነት የሚከናወነው በባለጉዳዮቹ መካከል ሲሆን፣ የፍርድ ሂደቱን በውክልና ማድረግ አይፈቀድም፡፡ ይህን ውል ሲቀበሉ፣ እርስዎና PDC በፍርድ ቤት የክስ ሂደት የመዳኘት መብታችሁን ወይም በውክልና የመዳኘት መብታችሁን ፈቅዳችሁ ለመተው እንደተስማማችሁ ይቆጠራል፡፡
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
በዚህ ውል የሚዋዋሉት ሁለቱም ወገኖች በዚህ ስምምነት ውስጥ ያላቸውን አንዱን መብት በማንኛውም ሁኔታ ሳይጠቀሙበት ቢቀሩ፣ በስምምነቱ ውስጥ ያሉትን ሌሎችን መብቶቻቸውን መጠቀም እንደማይችሉ ተደርጎ መቆጠር የለበትም፡፡
እርስዎ የ PDC ተቀጣሪ ሰራተኛ፣ ኤጀንት፣ ሸሪክ ወይም ባለድርሻ አባል አለመሆንዎን እንዲሁም በማንኛውም ሁኔታ PDCን በአስገዳጅ ሁኔታ እንዲስማማ ለማድረግ የሚያስችል ስልጣን እንደሌለዎት አውቀው ተስማምተዋል፡፡
በዚህ ውል የተጠቀሱትን የ PDC ግዴታዎች ከአቅሙ በላይ በሆኑ ጉዳዮች ለምሳሌ በሜካኒካል፣ ኤሌክትሮኒክ፣ ወይም በኮሚዩኒኬሽን መበላሸት ወይም መቋረጥ (በመብራት ኃይል መዋዠቅ የሚፈጠርን ጨምሮ) በሚፈጠሩ ችግሮች ምክኒያት ግዴታዎቹን ለመወጣት ሳይችል ቢቀር PDC በህግ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
በዚህ ስምምነት ውስጥ ያለ ማንኛውም ዓይነት ደንብ ትክክል ባይሆን ወይም ሕጋዊ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው ቢረጋገጥ፣ ተፈጻሚ የማይሆነው ይህ ደንብ ተወግዶ ቀሪው የስምምነቱ ክፍል ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የሚደረግ እና በህግ በኩልም ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡
የአገልግሎታችን ተጠቃሚው ሰው ይህን ስምምነት ከ PDC የፅሁፍ ፍቃድ ሳያገኝ ለሌላ አካል ማስተላለፍ ወይም ለሌላ አካል ፍቃድ መስጠት አይችልም፡፡ ነገር ግን ይህን ስምምነት፣ እንዲሁም PDC ያለውን መብቱን እና ግዴታውን በሙሉ የተጠቃሚውን ፍቃድ ወይም ስምምነት ሳይጠይቅ ለሌላ አካል ማስተላለፍ እንዲሁም መወከል ይችላል፡፡
ይህ ስምምነት (ተጠቃሚው በሚሰራቸው ተግባራት ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች፣ ወይም ይህ ስምምነት በሚፀናበት ጊዜ ተግባራዊ የሚሆኑ ማንኛውም የ PDC ህጎች፣ ደንቦች፣ ወይም መመሪያዎች፣ እንዲሁም ተጠቃሚው አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ካደረገበት ፕላትፎርም ላይ ያሉትን መመሪያዎች እና ህጎች ጨምሮ) በሁለቱም ወገኖች ማለትም በተጠቃሚው እና አገልግሎቱን በሚያቀርበው ድርጅታችን መካከል ያለ ሙሉ ስምምነት መሆኑን ሁለቱም ወገኖች ይስማማሉ፡፡ በዚህ ስምምነት እና ከዚህ በፊት በነበረው ስምምነት ወይም መመሪያ መካከል ልዩነት ወይም ተቃርኖ ቢኖር፣ ተፈጻሚነት የሚኖራቸው የዚህኛው ስምምነት ህግጋቶች እና መመሪያዎች ናቸው፡፡ በዚህ ስምምነት ውስጥ የተጠቀሰ ካልሆነ በስተቀር፣ ሁሉም ለውጦች በፅሁፍ ሆነው በሁለቱም አካላት ሊፈረምባቸው ይገባል፡፡