የ Premise የግላዊነት መመሪያ  

በስራ ላይ የሚውልበት ቀን፡ አፕሪል 1፣ 2024

የእርስዎ የግል መረጃዎች በምን መልኩ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ማወቅ እንደሚፈልጉ Premise Data Corporation (“Premise”) በትክክል ስለሚያውቅ፣ የእርስዎን መረጃዎች ሚስጢራዊነታቸውን ሁሌም እንጠብቃለን፡፡ ስለ እርስዎ የምንሰበስበውን፣ የምንጠቀመውን፣ እና ለሌሎች የምናካፍለውን የግል መረጃዎች ማወቅ ከፈለጉ ይህን ፅሁፍ እንዲያነቡ እንጋብዛለን፡፡ በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ፅሁፍ ውስጥ በጉልህ የተፃፉ ነገር ግን ትርጉማቸው ያልተቀመጡ ቃላቶችን ትርጉም በአጠቃቀም ውላችን ውስጥ ማንበብ ይችላሉ፡ https://tos.premise.com/terms-of-use/ 

ይህን አገልግሎት መጠቀም፣ ማለትም ድረ ገጻችንን፣ ፖርታል ወይም ደግሞ የኛን ፕላትፎርሞች፣ ወይም አፕሊኬሽናችንን ዳውንሎድ ማድረግ፣ በጥናቶቻችን መሳተፍ ወይም ደግሞ ጥናቶችን መመልከት (በአጠቃቀም ውላችን ላይ እንደተገለፀው) እና የ Premise Wallet ዋሌትን መጠቀም፣ በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ውስጥ የተገለፁትን ፖሊሲዎች እና ደንቦች እንደተቀበሉ፣ የእርስዎን የግል መረጃዎች ማለትም ምስሎች፣ የድምፅ ቅጂዎች፣ ቪዲዮዎች፣ ፎቶዎች እና ስክሪንሾቶች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት መሰብሰብ፣ መጠቀም እና ማካፈል እንድችል መፍቀድዎን ያረጋግጣል፡

የእርስዎን ሚና መረዳት

ከ Premise አገልግሎቶች ጋር ያላቸውን ዝምድና ለመግለፅ፣ በዚህ ፖሊሲ ውስጥ “ደንበኛ”፣ “ተሳታፊ” እና “ጎብኚ” የሚሉ ቃላቶችን Premise ይጠቀማል፡፡ ሚናዎቹ እንደሚከተለው ተዘርዝረው ተቀምጠዋል፡ 

    • ደንበኛ: ከድርጅታችን ጋር የገቡትን የደንበኝነት ውል ወይም ስምምነት (“የደንበኝነት ውል”) የሚያስፈፅም ግለሰብ (ወይም አገልግሎታችንን ለመጠቀም ውል የፈፀመ ድርጅት ሰራተኛ/አማካሪ ሆነው የእኛን አገልግሎት ለማግኘት ድርጅትዎ ስልጣን የሰጠዎት ግለሰብ ከሆኑ)፣ ወይም ደንበኞች ብቻ እንዲጠቀሙባቸው ታስቦ የተዘጋጁ የኦንላይን ፖርታሎች ወይም ገፆችን እንዲጎበኙ ከ Premise ፍቃድ የተሰጠዎት ግለሰብ ከሆኑ፣ በዚህ የግላዊነት መመሪያ ውስጥ ደንበኛ ተብለው ይጠራሉ፡፡ 
    • ተሳታፊ: የሞባይል አፕሊኬሽናችንን በስልካቸው ላይ የጫኑ  ማንኛውም ሰዎች፣ በዚህ የግላዊነት መመሪያ ውስጥ ተሳታፊ ተብለው ይጠራሉ፡፡
    • ጎብኚ: ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ የሆኑ ሰዎች በሙሉ ጎብኚ ተብለው ይጠራሉ፡፡

በዚህ የግላዊነት መመሪያ ክፍል I ላይ የተዘረዘሩት ስምምነቶች በሁሉም ደንበኞች፣ ተሳታፊዎች እንዲሁም ጎብኚዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ በክፍል II ላይ የተገለፀው ስምምነት በደንበኞቻችን ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ተሳታፊ ከሆኑ ደግሞ በክፍል III ላይ የተቀመጠው ስምምነት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ክፍል IV ላይ የተቀመጠው ስምምነት ደግሞ ተግባራዊ የሚደረገው በካሊፎርኒያ በሚኖሩ ተሳታፊዎች፣ ደንበኞች እና ጎብኚዎች ላይ ነው፡፡

ክፍል I – በማንኛውም ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ስምምነት – ደንበኞች፣ ተሳታፊዎች፣ እና ጎብኚዎች

ይህ የግላዊነት መመሪያ በ Premise አፕሊኬሽን፣ ድረገፅ፣ ፕላትፎርም፣ ምርት እና በአፕሊኬሽናችን፣ በድረገጻችን፣ ወይም በኦንላይን ፖርታሎቻችን አማካኝነት በሚቀርቡ ማንኛውም አገልግሎቶቻችን ላይ ተፈፃሚ ነው፡፡ የሞባይል አፕሊኬሽናችንን በስልክዎ ላይ ሲጭኑ፣ እንዲሁም በኦንላይን አገልግሎቶቻችን (ማለትም በድረገጻችን፣ ፖርታል እና ፕላትፎርሞቻችን) አማካኝነት ከእኛ ጋር ሲወያዩ፣ የ Premise ድርጅት ስለ እርስዎ መረጃዎችን ይሰበስባል፡፡ አገልግሎቶቻችንን በሚጠቀሙበት ማንኛውም ጊዜ ሁሉ የአጠቃቀም ውላችን ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፣ ስምምነቱም ይህን የግላዊነት መመሪያ ያካትታል፡፡ አገልግሎቱን የሚያቀርበው ድርጅት ወይም የአገልግሎቱ ባለቤት Premise ሲሆን፣ Premise መረጃዎችን በሚሰበስብበት እና በሚጠቀምበት ጊዜ ሁሉ ይህ የግላዊነት መመሪያ ተፈፃሚ ነው፡፡ 

በዚህ የግላዊነት መመሪያ ውስጥ የተገለፀውን መረጃ የምንልከው፣ የምናቀናብረው እና የምናስቀምጠው በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ሲሆን፣ ይህም ሃገር አሁን እርስዎ ከሚኖሩበት ሃገር አንፃር ሲታይ ያላት የመረጃ ጥበቃ ህግ ዝቀተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ካለ፣ የእርስዎን የግል መረጃ የተጠበቀ ለማድረግ በዚህ የግላዊነት መመሪያ በተጠቀሰው መልኩና ተግባራዊነት ካላቸው ሌሎች ህጎች አንፃር ተገቢውን እርምጃ እንወዳለን፡፡ 

በየጊዜው አገልግሎታችንን ለማሻሻል ጥረት እናደርጋለን፡፡ በመሆኑም በዚህ የስምምነት ውል ላይ በየጊዜው ማሻሻያ ሊደረግበት ይችላል፡፡ ለውጥ ሲኖር በአፕሊኬሽኑ አማካኝነት የፅሁፍ መልዕክት በመላክ፣ በሶሻል ሚድያ ገጾቻችን ላይ መረጃ ፖስት በማድረግ፣ እንዲሁም የተሻሻለውን የግላዊነት ፖሊሲ በድረገጻችን፣ ፕላትፎርሞቻችን፣ በፖርታሎቻችን እና በሌሎች ተገቢ በሆኑ መንገዶች በመጠቀም እናሳውቅዎታለን፡፡ ህግ ነክ ነገሮች ሲኖሩ ለእርስዎ እንድናሳውቅዎት የሚያስችለንን ፍቃድ ካልሰጡን (ወይም ደግሞ የኢሜል አድራሻዎን ባይሰጡንም እንኳን)፣ አገልግሎቶቻችንን በሚጠቀሙበት ጊዜ በስምምነቱ ላይ የተቀመጡት ህግጋቶች በእርስዎ ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፤ እንዲሁም ህጉን የማንበብ እና የመረዳት ኃላፊነት አለብዎት፡፡ ይህ የተሻሻለው የግላዊነት መመሪያ  ይፋ ከተደረገ ወይም ፖስት ከተደረገ በኋላ አገልግሎታችንን መጠቀም ከቀጠሉ፣ በመመሪያው ውስጥ በሚገኙ ውሎች ሁሉ ተስማምተዋል ማለት ነው፡፡ የምንሰበስበውን መረጃ የምንጠቀምበት፣ መረጃው በሚሰበሰብበት ጊዜ ተግባራዊ በሆነው የግላዊነት መመሪያችን መሰረት ነው፡፡ 

ገደብ እና ተፈፃሚነት  

ይህ የግላዊነት መመሪያ በየትኛውም ሃገር በሚኖሩ አገልግሎታችንን በሚጠቀሙ ግለሰቦች ላይ ሁሉ ተፈፃሚ ነው፡፡ 

ከ 18 አመት በታች ከሆኑ ሰዎች፣ ወይም ደግሞ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ የሆኑት ግለሰብ በሚኖሩበት ሃገር ከሚኖሩ አብዛኞች ሰዎች በእድሜ የሚያንሱ ከሆነ (በአጠቃላይ “ከሚፈቀደው ዝቅተኛ እድሜ በታች”) ከሆኑ ሰዎች እያወቅን መረጃ አንሰበስብም ወይም መረጃ እንዲሰጡን አንጠይቅም፡፡ እባክዎ እድሜዎ ከሚፈቀደው በታች ከሆነ አገልግሎታችንን መጠቀምም ሆነ የግል መረጃዎችን መላክ የለብዎትም፤ እንዲሁም እድሜያቸው ከ 13 አመት በታች ወይም ከሚፈቀደው እድሜ በታች የሆኑ ሰዎችን የግል መረጃ መላክ የለብዎትም፡፡ ከሚፈቀደው የእድሜ ክልል ወይም ከ 13 አመት በታች ከሆነ ሰው የግል መረጃ እንደሰበሰብን ከደረስንበት፣ ይህን የግል መረጃ በተቻለው ፍጥነት ከሲስተማችን ላይ እናስወግደዋለን፡፡ ከሚፈቀደው የእድሜ ክልል በታች የሆነ ሰው የግል መረጃ እንደላከልን የሚያውቁ ከሆነ፣ ወይም ሌላ ሰው ከሚፈቀደው እድሜ ወይም ከ 13 አመት በታች የሆነን ግለሰብ የግል መረጃን እንደሰጠን ካወቁ፣ እባክዎ በዚህ አድራሻ [email protected] ያሳውቁን፡፡

መረጃ አሰባሰብ እና አጠቃቀም

አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ የምንሰበስበው መረጃዎችን በተመለከተ

አገልግሎታችንን እንዴት እንደሚጠቀሙ፣ የእርስዎን ምርጫዎች፣ እና በአፑ ሴቲንግ ውስጥ የሚመርጡትን ምርጫዎችን በተመልከተ መረጃ እንሰበስባለን፡፡ መረጃ ለመሰብሰብ ኩኪዎችን፣ ፒክስል ታግ በማድረግ፣ እንዲሁም ልዩ የሆኑ የመለያ ቴክኖሎጂዎችን ልንጠቀም እንችላለን፡፡ በሚጠቀሙበት ብሮውዘር ወይም ስልክ ላይ በምናስቀምጣቸው ኩኪዎች አማካኝነት፣ ከእኛ አፕሊኬሽን ወይም ድረገጾች ከወጡ በኋላ ያለውን የኦንላይን አጠቃቀምዎን መረጃ ልንሰበስብ እንችላለን፡፡ ይህ የምንሰበስበው መረጃ፣ የግላዊነት መመሪያችንን መሰረት ባደረገ መልኩ ለእርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎት ለማሻሻል እና ለእርስዎ የተመጠነ እንዲሆን ለማድረግ ያስችለናል፡፡ 

በተጨማሪም እርስዎ በቀጥታ የሚሰጡንን እንዲሁም ደግሞ የሶስተኛ ወገን አገልግሎቶችን ለመጠቀም ከከፈቷቸው አካውንቶች አማካኝነት የምናገኘውን መረጃ እንሰበስባለን፡፡

የሚጠቀሙበት ብሮውዘር በየጊዜው የሚያከናውኑትን የኢንተርኔት አጠቃቀም እንቅስቃሴ የድረገፅ አስተዳዳሪዎች እና የኦንላይን አፕሊኬሽን እንዲሁም አገልግሎቶች (እንቅስቃሴዎን በማጥናት የማስታወቂያ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡትን ጨምሮ) መከታተል እንዳይችሉ “Do Not Track” የሚል አማራጭ ሊያቀርብልዎት ይችላል፡፡ ነገር ግን በዚህ ሰዓት የእኛን አገልግሎቶች በሚጠቀሙበት ጊዜ “Do Not Track” የሚለውን አማራጭ መጠቀም ስለማይችሉ፣ በመሆኑም የእኛን አገልግሎቶች ሲጠቀሙም ይሁን ከእኛ አፕሊኬሽን እና ድረገጾች ከወጡ በኋላ የሚያደርጉትን የኦንላይን እንቅስቃሴ መረጃ እንሰበስባለን፡፡ አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ፣ እነዚህን መረጃዎች መሰብሰብ እንድንችል ፈቃድ ሰጥተውናል ማለት ነው፡፡

ከ Premise ጋር የሚሰሩ እንደ Google፣ Bing፣ የሶሻል ሚዲያ ማስታወቂያ አገልግሎቶች፣ እና ተመሳሳይ አገልግሎቶች የእኛን አፕሊኬሽን እና ድረገጾች እንዲሁም በሌሎች አፕሊኬሽኖች አማካኝነት ስለ እርስዎ የግል መረጃዎችን መሰብሰብ/መቀበል ይችላሉ፡፡ ይህንም መረጃ ለአጠቃቀም መለኪያ እና ለማስታወቂያ አገልግሎቶች ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ ለማስታወቂያ ማሳለጫ የሚሆን መረጃ መሰብሰብ እና መጠቀም እንድንችል ፈቅደውልናል ማለት ነው፡፡ የ Google አናሊቲክስን አገልግሎት ካልፈለጉ እባክዎ በዚህ ሊንክ https://tools.google.com/dlpage/gaoptout/ ያለውን add-on በመጠቀም ምርጫውን ያስተካክሉ፡፡  

የአገልግሎት ተጠቃሚዎቻችንን የአጠቃቀም ሂደት ለማጥናት የአናሊቲክስ ሰርቪስ እንጠቀማለን፡፡ የአገልግሎታችን ተጠቃሚዎች የእኛን ሰርቪስ በየስንት ጊዜው እንደሚጎበኙ፣ የሚጎበኟቸውን ገጾች፣ እንዲሁም የእኛን አገልግሎት ከመጠቀምዎ በፊት የጎበኙትን አገልግሎት መረጃዎች ለመሰብሰብ Google Analytics ኩኪዎችን ይጠቀማል፡፡ ከ Google Analytics የምናገኘውን መረጃ፣ አገልግሎታችንን ለማሻሻል እንዲሁም አገልግሎታችንን የሚመለከቱ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማድረግ እንጠቀምበታለን፡፡ Google Analytics የሚሰበስበው አገልግሎታችንን በሚጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎን መሳሪያ IP አድራሻ እንጂ የእርስዎን ስም ወይም የግል መረጃዎች አይደለም፡፡ ከ Google Analytics የምናገኘውን መረጃ ከእርስዎ የግል መረጃ ጋር አናያይዘውም፡፡ Google Analytics እርስዎን ለመለየት ቋሚ የሆኑ ኩኪዎችን የሚጠቀም ቢሆንም፣ ይህን ኩኪ ከ Google ውጪ ማንም አይጠቀምበትም፡፡ አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ በ Google Analytics አማካኝነት Google የሚሰበሰበው መረጃ አጠቃቀም እና ማጋራት በ Google Analytics የአጠቃቀም ውል እና የግላዊነት መመሪያ መሰረት የሚከናወን ነው፡፡ ስለ Google Analytics ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ፡ http://www.google.com/policies/privacy/partners/፡፡

በጣም መሰረታዊ ያልሆኑ ኩኪዎችን ህጋዊ በሆነ መንገድ መጠቀም በሚያስገልገን ጊዜ፣ በኩኪ ማስተዳደሪያ ዘዴያችን አማካኝነት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን፡፡  

ተጨማሪ መረጃ

ስለምንሰበስባቸው ተጨማሪ መረጃዎች ኢንፎርሜሽን ለማግኘት ከዚህ በታች ያለውን የግላዊነት መመሪያ ክፍሎች ያንብቡ፡፡

መረጃ ማስቀመጥን በተመለከተ

የሰበሰብነውን የእርስዎን የግል መረጃ የምንጠቀምበት መረጃውን ለተሰበሰበበት ዓላማ ሲሆን፣ በተጨማሪም አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ ለህጋዊ፣ ለቁጥጥር፣ ግብር፣ አካውንቲንግ ወይም ለሪፖርት አላማ ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡ ቅሬታ ወይም ደግሞ ከእርስዎ ጋር የፍርድ ሂደት ውስጥ የሚያስገባ ጉዳይ እንዳለ ከተገነዘብን፣ አስፈላጊ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ የግል መረጃዎን ሲስተማችን ላይ ልናስቀምጠው እንችላለን፡፡ የግል መረጃዎች በእኛ ሲስተም ላይ ተቀምጠው የሚቆዩበትን ጊዜ የምንወስነው የተለያዩ ጉዳዮችን በማጤን ሲሆን፣ ይህም የግል መረጃውን መጠን፣ ባህርይ፣ እና ሚስጢራዊነት፣ ያለፍቃድ የእርስዎ የግል መረጃ ጥቅም ላይ ቢውል የሚፈጥረውን ችግር በማጤን፣ እና የግል መረጃዎን ለምንጠቀምበት ዓላማ እንዲሁም ይህን ዓላማ በሌላ መንገድ ማሳካት የምንችል ከሆነ፣ እንዲሁም የህግ፣ ቁጥጥር፣ ግብር፣ አካውንቲንግ ወይም ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ያካትታል፡፡ 

ይህ ክፍል ደግሞ በአውሮፓ ኢኮኖሚክ ኤሪያ (“EEA”) እና በዩናይትድ ኪንግደም (“UK”) ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች የግል መረጃ አሰባሰብ፣ አቀባበል፣ እና አቀነባበር ዙሪያ የሚገልፅ ነው፡፡ 

የግል መረጃዎን ተግባራዊነት ባላቸው ሕጎች ማለትም በ General Data Protection Regulation (Regulation (EU) 2016/679) (“EU GDPR”), የኢንግላንድ እና ዌልስ EU GDPR ሕግ፣ የስኮትላንድ እና ሰሜን አየርላንድ European Union Withdrawal Act 2018 (“UK GDPR”) ክፍል 3፣ የ UK Data Protection Act 2018 እና Privacy and Electronic Communications (EC Directive) Regulations 2003 (the “European Data Privacy Laws”) አማካኝነት መሰረት እንጠብቃለን እንዲሁም አገልግሎት እናውላለን፡፡ 

የምናቀናብራቸው የግል መረጃዎች አይነት፣ የምንከተለው ሕግ እና መረጃዎን በምን መልኩ እንደምናካፍል ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡ 

በአውሮፓ የመረጃ ግላዊነት ሕግ መሰረት፣ እርስዎ የሚከተሉት መብቶች አሉዎት፡ 

    • የግል መረጃዎን መቀበል 
    • የእርስዎን የግል መረጃዎች እንዲስተካከል መጠየቅ 
    • የእርስዎ የግል መረጃዎች ከሲስተማችን ላይ እንዲጠፋ መጠየቅ 
    • የግል መረጃዎ እንዳይቀናበር ተቃውሞ ማቅረብ 
    • የግል መረጃዎ ቅንብር የተገደበ እንዲሆን መጠየቅ
    • የግል መረጃዎን ማግኘት እንዲችሉ ወይም ለሶስተኛ ወገን እንዲሰጥ መጠየቅ
    • የግል መረጃዎን እንድናቀናብር የሰጡንን ፍቃድ በማንኛውም ሰዓት ላይ እንዲቋረጥ የማድረግ 

ከላይ የተዘረዘሩትን መብቶች መጠቀም ከፈለጉ ከዚህ በታች ባሉት መገናኛ መረጃዎች መሰረት ያነጋግሩን፡፡ የጠየቁት ነገር ውስብስብ እስካልሆነ እና ረጂም ጊዜ የሚወስድ ሆኖ እስካላገኘነው ድረስ፣ ለጥያቄዎ በአንድ ወር ውስጥ መልስ ያገኛሉ፡፡ የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ እና የጠየቁት መረጃን ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ለማረጋገጥ (መብትዎን እንዲያገኙ ለማድረግ) ተጨማሪ መረጃዎችን ልንጠይቅዎት እንችላለን፡፡ ከአውሮፓ የመረጃ ግልዊነት ሕግ አንፃር ማግኘት የሚችሉት እና የማይችሉት መብት እንዳለ መረዳት ይኖርብዎታል፡፡ ማለትም የሰጡን መረጃ እንዲቀናበር ፍቃድ ሰጥተውን ነገር ግን ያን ፍቃድ በሌላ ጊዜ ከሰረዙት በኋላ ቢሆንም እንኳን፣ ሕጉ በሚፈቅድልን መሰረት በሌላ ጊዜ መረጃውን ልንጠቀምበት የምንችል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ 

በ EEA ወይም UK ውስጥ የምናቀናብራቸውን የግል መረጃዎን፣ ከ  EEA ወይም UK ውጪ እንዲሁም አሜሪካን ጨምሮ ልንልክ እንችላለን፡፡ የግል መረጃዎ ከ EEA ወይም UK ውጪ የሚላከው፣ የአውሮፓ የመረጃ ግላዊነት ሕግ ወይም የዩናይትድ ኪንግደም ኢንፎርሜሽን ኮሚሽነር ወይም የአውሮፓ ኮሚሽን ወይም ስልጣን ያለው አካል በሚፈቅደው የአሰራር ደንብ መሰረት ብቻ ነው፡፡ 

ያነጋግሩን 

በዚህ የግላዊነት መመሪያ ላይ ጥያቄ ካለዎት፣ በዚህ [email protected] ኢሜል ወይም ደግሞ በዚህ አድራሻ Premise Data Corporation, Inc., Attn: Legal, 405 W 13th Street, 3rd Floor, New York, NY 10014, United States of America ወይም ደግሞ ከዚህ በታች በተቀመጡት የዳታ ፕሮቴክሽን ተወካዮች አማካኝነት ይጻፉልን፡፡  

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የእርስዎን ወይም የሌላ ስልጣን ያለው አካል ጥያቄን እኛን ወክለው በ UK እና EEA ውስጥ መቀበል የሚችሉ በእኛ በኩል የተወከሉ አካላት መሆናቸውን እናሳውቃለን፡ 

    1. United Kingdom:
      Adam Brogden [email protected]
      Tel +44 1772 217800
      1st Floor Front Suite
      27-29 North Street, Brighton
      England
      BN1 1EB
    2. European Economic Area:
      Adam Brogden [email protected]
      Tel +35315549700
      INSTANT EU GDPR REPRESENTATIVE LTD
      Office 2,
      12A Lower Main Street, Lucan Co. Dublin
      K78 X5P8
      Ireland

ለጥያቄዎ ተገቢ መልስ ካላገኙ ወይም ደግሞ አስፈላጊ ሆኖ ካገኙት፣ በአውሮፓ መረጃ ግላዊነት ሕግ መሰረት ለሚመለከተው የ UK ወይም EEA መረጃ ጥበቃ ባለስልጣን ቅሬታ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የዩናይትድ ኪንግደም ኢንፎርሜሽን ኮሚሽነር ቢሮ መረጃዎችን በዚህ ሊንክ ያገኛሉ http://www.ico.org.uk ፡፡    

ክፍል II – ተጨማሪ ውሎች ለደንበኞቻችን

ከላይ በክፍል I ከተጠቀሱት ስምምነቶች በተጨማሪ፣ ከዚህ በታች በክፍል II የተገለፀው ውል በደንበኞቻችን ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ 

በዚህ የግላዊነት መመሪያ እና በደንበኞች ውል መካከል ተቃርኖ ከተፈጠረ፣ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት የደንበኞች ውሉ ላይ የተጠቀሱት ስምምነቶች ተግባራዊ የሚሆኑ ሲሆን፣ ይህም የሚሆነው የደንበኞች ውል በስራ ላይ በሚውልበት ጊዜ ነው፡፡

መረጃ አሰባሰብ እና አጠቃቀም   

ለደንበኞች የተዘጋጁ የ Premise ብሮውዘር አፕሊኬሽኖች የሎግ ኢን፣ ኦቶንቲኬሽን፣ እንዲሁም የአካውንት መረጃዎችን ይሰበስባል፡፡ Sentry፣ Amplitude እና FullStory የተባሉ ከ Premise ጋር የሚሰሩ ካምፓኒዎች የእርስዎን የኦንላይን አጠቃቀም መረጃ እና የ Premise የደንበኞች አፕሊኬሽን አጠቃቀም መረጃን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህ መረጃ ጥቅም ላይ የሚውለው ደንበኞቻችን የ Premise አፕሊኬሽኖችን በተሻለ መንገድ መጠቀም እንዲችሉ ለማስቻል ሲሆን፣ ነገር ግን መረጃው ለሶስተኛ ወገን አይሸጥም፡፡ 

የሽያጭ መረጃ፣ ውይይቶች፣ እንዲሁም በጋራ የምንሰራባቸው መረጃዎች የሚቀመጡት እንደ Salesforce፣ Google Workspace፣ Microsoft 365 እና በሌሎች ጥብቅ እና የተለዩ በሆኑ ተስማሚ የፋይናንስ እና የውይይት ሶፍትዌሮች አማካኝነት ሲሆን፣ እነዚህንም ሲስተሞች ማየት የሚችሉት ስልጣን ያላቸው የ Premise ሰራተኞች ብቻ ናቸው፡፡ 

ክፍል III – ተጨማሪ ስምምነቶች ለተሳታፊዎች

ከላይ በክፍል I የተገለፁትን ጨምሮ ከዚህ በታች በክፍል III ያሉት ውሎች በተሳታፊዎቻችን ላይ ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡ 

 

የ Premise ሞባይል አፕሊኬሽኖች እርስዎ በሚኖሩበት አካባቢ ስለሚገኙ የተለያዩ ነገሮች መረጃ የሚሰበስቡ አፕሊኬሽኖች ናቸው፡፡ የ Premise አፕሊኬሽኖችን ዳውንሎድ ካደረጉ ወይም ደግሞ የ Premise ዋሌት አገልግሎትን ለመጠቀም ከተመዘገቡ፣ በዚህ የግላዊነት መመሪያ ውስጥ በተገለፀው መልኩ የእርስዎን የግል መረጃዎን (ማለትም ምስሎች፣ ቪዲዮዎች፣ የድምፅ ቅጂዎች፣ ፎቶዎች፣ ስክሪንሾቶች) መሰብሰብ፣ መጠቀም፣ ማጋራት፣ እንዲሁም መሸጥ እንድንችል ፍቃድ እንደሰጡን ይቆጠራል፡፡ በተጨማሪም Premise የእርስዎን መረጃዎች እና የመረጃ ትንተናዎች እንዲሁም በጥናቶቻችን የምንሰበስበውን መረጃ ለደንበኞቹ አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዲውል መስጠት እንዲችል ፍቃድ ሰጥተዋል ማለት ነው፡፡ 

 

መረጃ መሰብሰብን በተመለከተ 

የምንሰበስባቸውን መረጃዎች ዓይነት እና ለምን እንደምንሰበስብቸው፣ እንዲሁም ከአውሮፓ የመረጃ ግላዊነት ሕግ አንጻር ያለውን አግባብነት ከዚህ በታች ዘርዝረናቸዋል፡፡ ቀጥሎ በቀረበው የግላዊነት መመሪያ ክፍል ስለምንሰበስበው የግል መረጃ ተጨማሪ ማብራሪያ እናቀርባለን፡፡ ከታች ባቀረብናቸው የህግ አግባቦች ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች ካስፈለገዎት ያነጋግሩን፡፡

የምሰበስበው መረጃ  የምንሰበስብበት ዓላማ የሕግ አግባብነት (በአውሮፓ የመረጃ ግላዊነት ሕግ መሰረት)
መለያዎችን ለምሳሌ ስም፣ ኢሜል አድራሻ፣ የኢንተርኔት መለያ (ለምሳሌ ዩዘር ኔም ወይም የተጠቃሚ ስም)፣ በሞባይል ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች አማካኝነት የሚሰጡ በተጠቃሚዎች መስተካከል የሚችሉ መለያዎች፣ ፓስወርድ፣ ዲጂታል ፊርማዎች እርስዎን ለመለየት፣ የሰሯቸውን ተግባራት ለመለየት፣ አካውንትዎን በተመለከተ ከእርስዎ ጋር ለመነጋገር፣ ስለጥናቶች እና አገልግሎቶች አዲስ መረጃ ለመስጠት፣ አገልግሎታችንን ለማስቀጠል፣ እንቅስቃሴዎችን ለማጥናት እና የአገልግሎት አሰጣጥ እና የመለየት ስራዎችን ለማሻሻል፣ ለደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን መረጃዎችን ለማጠናቀር፣ እንዲሁም የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመቀነስ፡፡ 
  • ከእርስዎ ጋር ውል ለመያዝ 
  • ለሕጋዊ አላማዎች 
  • ሕግ ለማክበር (ማጭበርበርን ለመከላከል) 
ምስሎች፣ ቪዲዮና የድምፅ፣ የፎቶ እና የስክሪንሾት ቀረፃዎችን፣   እርስዎን ለመለየት፣ የሰሯቸውን ተግባራት ለመለየት፣ አካውንትዎን በተመለከተ ከእርስዎ ጋር ለመነጋገር፣ ስለጥናቶች እና አገልግሎቶች አዲስ መረጃ ለመስጠት፣ አገልግሎታችንን ለማስቀጠል፣ እንቅስቃሴዎችን ለማጥናት እና የአገልግሎት አሰጣጥ እና የመለየት ስራዎችን ለማሻሻል፣ ለደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን መረጃዎችን ለማጠናቀር፣ እንዲሁም የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመቀነስ፡፡ 

ይህም ማለት የሚሰጡን ምስሎች፣ ቪዲዮዎች፣ የድምፅ ቅጂዎች፣ ስክሪንሾቶች በሌላ ሶስተኛ አካል (የኛ ወይም የሌሎች ደንበኞች በሆኑ አካላት) አማካኝነት በሶሻል ሚዲያዎች ላይ ፖስት ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ 

  • ለሕጋዊ አላማዎች 
  • ሕግ ለማክበር (ማጭበርበርን ለመከላከል) 
  • ፍቃድ 
ቦታ  በጥናቶቻችን መሳተፍ ያለባቸውን ተጠቃሚዎች ለመለየት፣ ለደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን መረጃዎችን ለማጠናቀር፣ ተጠቃሚዎች የሚሰጡንን የቦታ መረጃ በማጣራት የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመቀነስ፡፡  
  • ለሕጋዊ አላማዎች 
  • ሕግ ለማክበር (ማጭበርበርን ለመከላከል) 
  • ፍቃድ 
የተጠቃሚው ስልክ ወይም ኮምፒውተር መለያ እና IP አድራሻ፣ ለምሳሌ ኦፐሬቲንግ ሲስተም፣ ዩዘር ሴቲንጎች እና የአገልግሎታችን አጠቃቀም  የተጠቃሚውን አይነት እና የሚኖሩበትን ቦታ መሰረት ያደረጉ ይዘቶችን ማቅረብን ጨምሮ አገልግሎታችንን ለተጠቃሚዎች የተመጠነ ለማድረግና ለማሻሻል፣ 
  • ለሕጋዊ አላማዎች 
  • ፍቃድ
የስልክ ወይም ኮምፒውተር መረጃ  አፕሊኬሽኑን ለማሻሻል ወይም በአፑ ውስጥ ችግር ሲፈጠር የተጠቃሚውን ነባራዊ ሁኔታ ለመረዳት፣ ለደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን መረጃዎችን ለማጠናቀር፣ ክፍያ ያላቸውን ጥናቶች በሚሰሩበት ጊዜ ቅሬታ ቢፈጠር አለመግባባቱን ለመፍታት የሚያስችል መረጃ ለመሰብሰብ፡፡  
  • ከእርስዎ ጋር ውል ለመያዝ 
  • ለሕጋዊ አላማዎች 
ቋንቋ ተጠቃሚው በሚረዳው ቋንቋ አማካኝነት የተዘጋጁ ይዘቶችን ለተጠቃሚው በአፑ ውስጥ ለማረቅረብ እንድንችል፡፡ 
  • ከእርስዎ ጋር ውል ለመያዝ 
  • ለሕጋዊ አላማዎች 
የኤፒአይ አሰራር መለኪያዎች አፑ የሚጠቀምባቸው ሁሉም ኤፒአይ በትክክል እንደሚሰሩ በማረጋገጥ ተጠቃሚው አፕሊኬሽኑን በተሻለ ሁኔታ እንዲጠቀሙበት ማስቻል፡፡ 
  • ከእርስዎ ጋር ውል ለመያዝ 
  • ለሕጋዊ አላማዎች 
የአፕሊኬሽን ስሞች  ለአፕሊኬሽኑ በትክክል መስራት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለምሳሌ የቦታ መረጃ፣ ሰዓት ወዘተ የሚለውጥ ወይም የሚቀይር አፕሊኬሽኖችን ተጠቃሚዎች አለመጠቀማቸውን በማረጋገጥ የማጭበርበር ድርጊቶችን መቀነስ፣ ለደንበኞቻችን እና ለአጋሮቻችን ትክክለኛ መረጃዎችን ለማቅረብ፡፡  
  • ለሕጋዊ አላማዎች 
  • ሕግ ለማክበር (ማጭበርበርን ለመከላከል) 
የባትሪ ሁኔታ አፕሊኬሽናችን በተጠቃሚው ስልክ ባትሪ ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለመረዳት፣ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመለየት እና ለመቆጣጠር፡፡  
  • ለሕጋዊ አላማዎች 
  • ሕግ ለማክበር (ማጭበርበርን ለመከላከል) 
ዋይፋይ እና ዳታ  ተጠቃሚው በስልካቸው ላይ ማግኘት የሚችሉትን የኢንተርኔት ፍጥነት በመረዳት አጋር ድርጅቶች የኔትወርክ አገልግሎታቸውን እንዲያሻሽሉ ማገዝ፣ እንዲሁም የኔትወርክ ጥንካሬን መሰረት በማድረግ የተሻለ አገልግሎት ማቅረብ፡፡ 
  • ለሕጋዊ አላማዎች 
የ Premise ዋሌት አገልግሎትን ለመጠቀም ከተመዘገቡ እነዚህ ተጨማሪ መረጃዎች እንሰበስባለን፡ 

  • የ Premise ተጠቃሚ መለያ
  • የ Premise ዋሌት መለያ 
  • የ PrimeTrust ኮንታክት መለያ
  • የሃገር እና የክልል ኮድ አካውንቱን ለመለየት
  • ሙሉ ስም
  • የትውልድ ቀን
  • የስልክ ቁጥር
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር 
  • አድራሻ 
  • የቀበሌ መታወቂያን የሚያሳይ ፎቶ 
  • የሚኖሩበትን አድራሻ የሚያሳይ ዶክመንት ፎቶ 
  • የእርስዎ ፎቶ 
  • የኤክስተርናል ክሪፕቶ ዋሌት አድራሻ (ከእኛ አገልግሎት ውጪ ወደሆነ አካውንት ገንዘብ የሚልኩ ወይም የሚያስቀምጡ ከሆነ) 
እርስዎን ለመለየት፣ የ Premise ዋሌት አገልግሎትን እና የእርስዎን የ Premise ዋሌት አካውንት ለማስተዳደር፣ ለማስቀጠል እና በትክክል እንዲሰራ ለማድረግ፣ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመቆጣጠር፣ የመንግስትን ህግ ለማክበር፣ ለ “ደንበኛዎን ይወቁ” አስፈላጊ ነገሮችን ለማሟላት፣ የኋላ ታሪክ ጥናቶችን ለማሳለጥ፣ የክፍያ ሂደትን ለማፋጠን፣ የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ እና ከአፑ ውጭ የሆኑ የክሪፕቶ ዋሌት አድራሻዎችን ለማረጋገጥ፣ እንዲሁም የክሪፕቶካረንሲ ግብይቶችን ለማፋጠን፡፡  
  • ከእርስዎ ጋር ውል ለመያዝ 
  • ለሕጋዊ አላማዎች 
  • ሕግ ለማክበር (ማጭበርበርን ለመከላከል) 

 

በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች የምንሰበስበው አገልግሎታችንን ለተጠቃሚዎች በተሻለ መልኩ ተደራሽ ለማድረግና በአገልግሎታችን ክፍያ ባላቸው ጥናቶቻችን ላይ ሆን ብለው ለማጭበርበር የሚሞክሩ ተሳታፊዎችን ለመከላከል፣ እንዲሁም ደግሞ ለደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን የተሟላ ፕሮጀክቶችን ለማቅረብ ነው፡፡ ይህ መረጃ ወደ Premise የሚላከው Amplitude በተባለ የሶስተኛ ወገን አናሊቲክስ ድርጅት አማካኝነት ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን የተወሰኑ መረጃዎች በከፊል ከእኛ ጋር ለሚሰሩ ድርጅቶች፣ ደንበኞቻችን እና ለአጋሮቻችን ልናካፍላቸው እንችላለን፡፡ 

ስለምንሰበስበው መረጃዎች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ቀጥለው ያንብቡ፡ 

እርስዎ ለኛ የሚሰጡን መረጃ

እኛ የምንሰበስበው መረጃዎች እርስዎ በቀጥታ የሚሰጡንን እና በሚጠቀሙባቸው ሌሎች የሶስተኛ ወገን አካውንቶች አማካኝነት የሚሰጡንን መረጃዎች ነው፡፡ አካውንት ሲከፍቱ ወይም ሲያስተካክሉ፣ ተግባራቶችን ሲሰሩ፣ የደንበኞች ማዕከላችንን ሲያነጋግሩ፣ ወይም ከእኛ ጋር ሲነጋገሩ በሙሉ መረጃዎችን እንሰበስባለን፡፡ የምንሰበስበው መረጃም የእርስዎን ስም፣ የሶሻል ሚድያ አካውንት፣ ኢሜል፣ ስልክ ቁጥር፣ የክፍያ መለያ፣ እንዲሁም ሌሎችን ለመስጠት የተስሟሟቸውን መረጃዎች ነው፡፡ በተጨማሪም እርስዎ የሚሰጡንን ማንኛውንም ምስሎች፣ ቪዲዮ ወይም ቀረፃዎች፣ ማለትም ፎቶዎች፣ ስክሪንሾት እና የድምፅ ቀረፃዎች በሙሉ እንሰበስባለን፡፡

አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ የምንሰበስበው መረጃዎች

አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ እንዲሁም የ Premise ዋሌት አገልግሎትን ለመጠቀም ከተመዘገቡ፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመረጃ አይነቶች እንሰበስባለን፡

የቦታ መረጃ: የ Premise አገልግሎትን ተጠቅመው በጥናቶቻችን ሲሳተፉ፣ ጥናቱን የጀመሩበትን እና በጥናቱ የተጠየቀውን ነገር የሚገኝበትን ትክክለኛ ቦታ መረጃ እንሰበስባለን፡፡ በሞባይል ስልክዎ ኦፐሬቲንግ ሲስተም (“ፕላትፎርም”) ውስጥ በሚገኘው የፍቃድ ስርዓት አማካኝነት የስልክዎን ትክክለኛ መገኛ ቦታ ለማወቅ እንድንችል ፍቃድ ከሰጡን፣ አፕሊኬሽኑን ሲጠቀሙበትም ሆነ ከዘጉት በኋላ የስልክዎን ትክክለኛ መገኛ ቦታ የሚጠቁም መረጃ መሰብሰብ እንችላለን፡፡ ከሚጠቀሙበት ስልክ IP አድራሻ ተነስተን የእርስዎን መገኛ ቦታ መረጃ ማግኘትም እንችላለን፡፡

የስልክ ኮንታክት መረጃ: በሞባይል ስልክዎ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ውስጥ በሚገኘው የፍቃድ ስርዓት አማካኝነት የእኛ አፕሊኬሽን የእርስዎን የስልክ ኮንታክት ዝርዝሮች ማግኘት እንዲችል ፍቃድ ከሰጡን፣ አካውንትዎን ለማረጋገጥ፣ አፕሊኬሽኑን ለሌሎች ለማሳወቅ እና ተመሳሳይ አላማዎችን ለማሳካት እንድንችል የእርስዎን የስልክ ኮንታክቶች ስም ዝርዝር እና ስልክ ቁጥር መረጃ ልንይዝ እንችላለን፡፡

የስልክ ባትሪ መረጃ: በሞባይል ስልክዎ ፕላትፎርም ውስጥ በሚገኘው የፍቃድ ስርዓት አማካኝነት የእኛ አፕሊኬሽን የእርስዎን ስልክ የባትሪ ሁኔታ መረጃ ማግኘት እንዲችል ፍቃድ ከሰጡ፣ አፕሊኬሽኑ በምን ሁኔታ እንደሚሰራ ለማጥናት እንድንችል የስልክዎን የባትሪ መጠን እና የቻርጅ አደራረግ ሂደት መረጃ ልንሰበስብ እንችላለን፡፡  

የገንዘብ ማስተላለፍ ሂደት መረጃ: አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ የክፍያ መረጃዎችን፣ የተጠቀሙበትን የክፍያ ማስተላለፊያ መንገድ፣ ጥናት የሰሩበትን፣ ያስረከቡበትን፣ የተገመገመበትን እንዲሁም የጥናቱ የተከፈለበትን ቀን እና ሰዓት፣ ክፍያ ለማውጣት የሞከሩበትን ቀን፣ የሰሩትን አጠቃላይ ገንዘብ፣ እንዲሁም ሌሎችን ተመሳሳይ የገንዘብ ማስተላለፊ ሂደቶችን የሚመለከቱ መረጃዎችን እንሰበስባለን፡፡

የስልክ ቀፎ መረጃ: የስልክ ቀፎ ሞዴል፣ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና ቨርዥን፣ ሶፍትዌሮች፣ የፋይል ስሞች እና ቨርዥኖች፣ የሚመርጡትን ቋንቋ፣ ልዩ የስልክ መለያ ቁጥር፣ ለማስታወቂያ አላማ የሚሆኑ መለያዎች፣ ሴሪያል ቁጥር፣ የዲቫይስ ሞሽን መረጃ፣ እንዲሁም የሞባይል ኔትወርክ መረጃዎችን የመሳሰሉ መረጃዎችን እንሰበስባለን፡፡

የሎግ መረጃ: አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ እንደ ስልክ እና ኮምፒውተር IP አድራሻ፣ የጎበኙበትን ቀን እና ሰዓት፣ የጎበኙትን ገፅ ወይም የአፕሊኬሽን ክፍል፣ አፕሊኬሽኑ ክራሽ ሲያደርግ ወይም ተመሳሳይ የሲስተም ሁኔታዎችን፣ የተጠቀሙበትን ብሮውዘር፣ ወደኛ ገፅ ከመምጣትዎ በፊት የጎበኙትን የሶስተኛ ወገን አገልግሎት የመሳሰሉ የሰርቨር ሎግ መረጃዎችን እንሰበስባለን፡፡ በተጨማሪም ከኢንተርኔት እና ሌሎች የኦንላይን እንቅስቃሴዎችን፣ የብሮውዘር መረጃ እና የኢንተርኔት እንቅስቃሴ ታሪክ መረጃ፣ የኩኪ መረጃ (ፍቃድ የሰጧቸውን ኩኪዎች) እና የተጠቀሙበትን ጊዜ የሚያሳዩ መረጃዎችን እንሰበስባለን፡፡

ከሌላ ምንጮች የምንሰበስባቸው መረጃዎች 

የሚጠቀሙባቸውን የሶስተኛ ወገን አገልግሎት መረጃዎች ከሰጡን፣ ወይም ወደ አፕሊኬሽኑ ለመግባት የሶስተኛ ወገን ድረገፅ ወይም አገልግሎትን ተጠቅመው ከገቡ፣ በእነዚያ አካውንቶች (“የሶስተኛ ወገን አካውንት መረጃ”) ያሉዎት የተወሰኑ መረጃዎች እንዲተላለፉ ፍቃድ ከሰጡ፣ መረጃዎቹ ወደ Premise ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ደግሞ ወደኛ አገልግሎት የሚተላለፉ የሶስተኛ ወገን አካውንት መረጃዎች በዚህ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ የዚህን አፕሊኬሽን ወይም ድረገጽ መረጃ ከተጠቃሚው ማለትም ከእርስዎ መረጃ ጋ በማገናኘት ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡  

እንደ Google፣ Branch፣ Leanplum፣ Amplitude እና FullStory ያሉ ከ Premise ጋር የሚሰሩ አጋር ድርጅቶች የእርስዎን የግል መረጃ እና በተለያዩ ድረገጾች እና አፕሊኬሽኖች አማካኝነት ያለዎትን የኢንተርኔት አጠቃቀም እንቅስቃሴ መረጃ መሰብሰብ ወይም ከእኛ መቀበል ይችላሉ፡፡ ይህንም መረጃ ተግባራቶችን እና የዳሰሳ ጥናቶችን ለማረጋገጥ፣ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመከላከል፣ እንዲሁም የመለኪያ እና የማስታወቂያ አገልግሎቶችን ለማቅረብ እንድንችል ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡  

Premise የማጭበርበር ድርጊቶችን መከላከል እና ከህግ ጋር መስማማትን ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ተግባራት ናቸው፡፡ አገልግሎታችንን ለመጠቀም ብቁ መሆንዎን እና አፕሊኬሽኑን ተጠቅመው በጥናቶቻችን መሳተፍ እንደሚችሉ ለማረጋገጥ፣ Premise በራሱ ስልጣን የኋላ ታሪክ እና የደህንነት ምርመራዎችን ሊያከናውን ይችላል፡፡ 

የፕላትፎርም ፍቃዶችን የሚመለከቱ አስፈላጊ መረጃዎች   

የሚጠቀሙባቸው አፕሊኬሽኖች፣ በስልክዎ ቀፎ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ መረጃዎችን ያለ እርስዎ ፍቃድ ማግኘት እንደማይችሉ የሞባይል ፕላትፎርሞች በግልፅ አስቀምጠዋል፡፡ የእርስዎን ፍቃድ ለማግኘት እነዚህ ፕላትፎርሞች የተለያየ አይነት የፍቃድ ስርዓት አላቸው፡፡ የሚጠቀሙበት ስልክ ኦፐሬትንግ ሲስተም አንድሮይድ ከሆነ፣ የ Premise አፕሊኬሽንን ከመጠቀምዎ በፊት አፑ የሚፈልገውን ፍቃድ ይነግርዎታል፡፡ ከዚያ በኋላ አፕሊኬሽኑን መጠቀም ከቀጠሉ ፍቃድ ሰጥተዋል ማለት ነው፡፡

የመረጃ አጠቃቀም

ስለ እርስዎ የሰበሰብነውን መረጃ ማለትም ምስል፣ ቪዲዮ፣ ድምፀ ቅርፅ፣ ፎቶ፣ እና ስክሪንሾቶች የምንጠቀምበት ለሚከተሉት ጉዳዮች ነው፡  

    • አገልግሎታችንን ተደራሽ ለማድረግ፣ እና ለማሻሻል፣ የ Premise ዋሌት አገልግሎትን ለመጠቀም ከተመዘገቡ ደግሞ ክፍያን ለማፋጠን፣ የጠየቁትን ምርት እና አገልግሎት ለማቅረብ (ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ለመላክ)፣ አዳዲስ ፊቸሮችን ለመጨመር፣ ለተጠቃሚዎች የደንበኞች አገልግሎትን ለማቅረብ፣ የተጠቃሚዎችን ማንነት ትክክለኛነት ለማረጋገጥ፣ ስለምርቶቻችን እንዲሁም አስተዳደራዊ መልዕክቶች ሲኖሩ መረጃዎችን ለመላክ፤ 
    • የውስጥ ስራዎችን ለማከናወን፣ ለምሳሌ የ Premise ዋሌትን ጨምሮ አገልግሎታችንን ያላግባብ ከሚጠቀሙ ወይም የማጭበርበር ድርጊቶችን ከሚፈፅሙ ሰዎች ለመከላከል፤ የአሰራር እና አፕሊኬሽኑ ውስጥ ችግር ሲፈጠር ለመለየት፤ የመረጃ ትንተና፣ ሙከራ፣ እና ጥናት ለመስራት፤ የአጠቃቀም ሂደቶችን ለመገምገም እና ለመቆጣጠር፤ 
    • በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተደገፈ የመረጃ ትንተና ለደንበኞቻችን እና ለአጋር ድርጅቶቻችን ለመስጠት፣ 
    • ለአፕሊኬሽኑ ተጠቃሚዎች ጠቃሚ የሆነ መረጃ በሚኖርበት ጊዜ መረጃዎችን ለመላክ ወይም ከደንበኞች ማዕከል ባልደረቦቻችን ጋር የሚያደርጉትን ውይይት ለማስተናገድ፤ 
    • ለእርስዎ ይጠቅማሉ ብለን የምናስባቸው ስለ ምርቶቻችን፣ አገልግሎታችን፣ ፕሮሞሽን፣ ዜና፣ እንዲሁም ስለ Premise እና ሌሎች ድርጅቶች ዝግጅቶች መረጃዎችን ለመላክ፤ ውድድር፣ ሽልማት፣ እና ተመሳሳይ የፕሮሞሽን ሽልማቶችን ለማስተናገድ፤ 
    • የ Premise ዋሌትን ጨምሮ አገልግሎታችንን ለእርስዎ የተመጠነ ለማድረግ እና ለማሻሻል፣ ጠቃሚ ፊቸሮችን፣ ሪፈራሎችን፣ እንዲሁም ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ፡፡  

የግል መረጃዎን በህጋዊ መንገድ ለኮንትራት ወይም ለህጋዊ ዓላማ ማስፈፀሚያነት፣ የ Premise ዋሌትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎታችንን፣ ድረገጻችንን ለማስተዳደር እንዲሁም የቢዝነስ እና ማርኬቲንግ ስራችንን ለማሳካት፣ ለምርመራ ወይም አለመግባባቶችን ለመፍታት እንዲሁም ለማስታወቂያ አላማ ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡ የእርስዎን የግል መረጃ ተገቢ በሆነ መንገድ በምንጠቀምበት ጊዜ፣ ተፈጻሚነት ባለው የህግ መንገድ የእርስዎ የግል መረጃ አገልግሎት ላይ እንዳይውል የመቃወም መብት አለዎት፡፡  

መረጃን ማጋራት  

ከዚህ በታች የተዘረዘረውን ጨምሮ፣ ስለ እርስዎ የምንሰበስበውን መረጃ ማለትም ምስሎች፣ ቪዲዮ፣ የድምፅ ቅጂዎች፣ ፎቶዎች፣ ስክሪንሾቶች በዚህ የግላዊነት መመሪያ በተገለፀው መልኩ (የ Premise ዋሌት አገልግሎትን ጨምሮ)፣ ከመረጃው ትንተና የሚገኘውን ውጤት (የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ አውቶሜትድ አናሊቲክስ ጨምሮ) ወይም ደግሞ መረጃውን በምንሰበስብበት እና በምናጋራበት ጊዜ በተገለፀው መልኩ መረጃውን ለሌሎች ልናካፍል ወይም ልንሸጥ እንችላለን፡ 

    • የመረጃ መሰብሰብ/በስማችን የመረጃ ማጠናቀር ስራ ለሚሰሩልን ወይም ደግሞ የመረጃ ማከማቸት አገልግሎት ለሚሰጡን የ Premise ፓርትነሮች እና አጋር ድርጅቶች፤ 
    • መረጃ፣ ምስሎችን፣ ቀረጻና ቪዲዮዎችን፣ ፎቶ፣ ስክሪንሾት እና የድምፅ ቀረጻዎችን ጨምሮ፣ በዓለም ዙሪያ መረጃዎችን እንድንሰበስብላቸው ለጠየቁን የ Premise ደንበኞች፡፡ ይህም ማለት የሚያካፍሉን መረጃዎች፣ ምስሎች፣ ቪዲዮዎች፣ የድምፅ ቅጂዎች፣ ፎቶዎች እና ስክሪንሾቶች በሶስተኛ ወገኖች (ማለትም በደንበኞቻችን እና በእነርሱ ደንበኞች) አማካኝነት በሶሻል ሚዲያዎች ወይም በሌሎች ፕላትፎርሞች ላይ ፖስት ሊደረጉ ይችላሉ፤ 
    • ለድርጅታችን ስራ የሚሰሩ የተለያዩ ሻጮች፣ አማካሪዎች፣ የስራ አድቫይዘሮች፣ የማርኬቲንግ ፓርትነሮች፣ ኦዲተሮች፣ እንደ ፋይናንሺያል ወይም የህግ አማካሪዎች እና ስራቸውን ለመስራት እንዲህ አይነት መረጃዎችን ማግኘት ለሚያስፈልጋቸው ሌሎች አገልግሎት ሰጪዎች፤ 
    • በህግ አካላት እንዲህ አይነት መረጃዎችን እንድናቀርብ ስንጠየቅና መረጃውን ለመስጠት በህግ ና ደንብ የሚንጠየቅ ከሆነና እንዲሁም የፍርድ ቤት ጥሪ እና ትዕዛዝ ከደረሰን፤  
    • ህጋዊ መብቶችን ለማስከበር፣ ወይም ህጋዊ የሆኑ የይገባኛል ጥያቄዎች ሲነሱ ለመከላከል፤ 
    • ህገ ወጥ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ፣ የአጠቃቀም ውላችንን የሚጥሱ ተግባራት ሲከሰቱ፣ ወይም በአጠቃላይ ህግ የሚጥሱ ነገሮች ሲፈፀሙ ምርመራ ለማካሄድ፣ ለመከላከል እና እርምጃ ለመውሰድ፤ 
    • አሰራራችንን ህጋዊ ለማድረግ፣ የታክስ ህግን ጨምሮ፤ 
    • ፕሮሞሽን ወይም ሰርቬይ በሚኖርበት ጊዜ ለማከናወን፤ 
    • የአጠቃቀም ውላችንን እና መመሪያዎቻችንን ከጣሱ፣ የ Premiseን እንዲሁም የሌሎችን መብት ለማስከበር ለህግ አካላት፣ ለመንግስት ባለስልጣናት፣ ወይም ለሌላ ሶስተኛ ወገን ልንሰጥ እንችላለን፤ 
    • ድርጅቱ ከሌላ ድርጅት ጋር ከተዋሃደ፣ ከተሸጠ፣ ወይም የመዋቅር ለውጥ ካደረገ፣ ፈንድ ከተደረገ፣ ወይም የድርጅቱ ንብረት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለሌላ ድርጅት ባለቤትነቱ ከተላለፈ፤  
    • አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ መረጃዎን ለማካፈል እርስዎን ጠይቀንዎት (በአፑ ውስጥ ወይም በጥናቶቻችን)፣ እርስዎም ፍቃድ ከሰጡን፤ እና 
    • እርስዎን በተናጠል ለመለየት በማያስችል መልኩ መረጃዎችን አጠናቅረን ስም ሳንጠቅስ በምናቀርብበት ጊዜ፡፡ 

በሌሎች ድርጅቶች የሚቀርቡልን የአናሊቲክስ እና የአድቨርታይዚንግ አገልግሎቶችን በተመለከተ  

ሌሎች ድርጅቶች ከአገልግሎታችን ጋር ያላቸውን የአጠቃቀም ሂደት እንዲለኩልን፣ በስማችን ማስታወቂያዎችን እንዲሰሩልን፣ እንዲሁም የማስታወቂያዎችን ውጤት እንዲመዘግቡና ሪፖርት እንዲያደርጉልን ፍቃድ ልንሰጥ እንችላለን፡፡ እነዚህ ድርጅቶች እርስዎ የኛን አገልግሎቶችን እና ሌሎች ድረገጾችን እና የሌሎች አካላት ድረገጾች ሲጎበኙ የእርስዎን ስልክ ወይም ኮምፒውተር ለመለየት እንዲችሉ ኩኪዎችን፣ የዌብ ቤከኖችን፣ SDK፣ እንዲሁም ሌሎችን ተክኖሎጂዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡  

የእርስዎ ምርጫዎች 

የአካውንት መረጃ

በፈለጉት ጊዜ ወደ አፕሊኬሽኑ በመግባት የእርስዎን አካውንት መረጃዎችን ማስተካከል ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ህጉ በሚፈቅድልን መሰረት የተወሰኑ የእርስዎን መረጃዎች ለህጋዊ ወይም ለስራ ጉዳይ ልናስቀምጥ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ከአካውንትዎ ጋር የተገናኘ ያልተዘጋ ክሬዲት ወይም ዴቢት ካለ፣ ወይም ደግሞ የማጭበርበር ድርጊት ፈፅመው ወይም የአጠቃቀም ውላችንን ከጣሱ፣ አካውንትዎን ከሲስተማችን ላይ ከማጥፋታችን በፊት የተከሰተውን ችግር መፍታት ይኖርብናል፡፡

የአጠቃቀም መብት 

የአገልግሎታችን ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች በአጠቃቀም ዙሪያ ና ማስተካከያዎች፣ ወይም አካውንት እንዲጠፋላችው አሊያም ደግሞ የግል መረጃቸው ከሲስተማችን ላይ እንዲጠፋላቸው ጥያቄ ካቀረቡ፣ Premise ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ያስተናግዳል፡፡   

የቦታ መረጃ  

የ Premise ዋሌት አገልግሎትን ጨምሮ፣ የምናቀርበው አፕሊኬሽን የሚጠቀሙበትን የሞባይል ስልክ ኦፐሬቲንግ ሲስተም የፍቃድ ስርዓት በመከተል የስልክዎን ትክክለኛ መገኛ ቦታ ይመዘግባል፡፡ የስልክዎን ትክክለኛ መገኛ ቦታ ለመመዝገብ የሚያስችል ፍቃድ ካልሰጡን የአፕሊኬሽኑ አጠቃቀም የተገደበ ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ የስልክዎን መገኛ ቦታ እንድናውቅ የሚያስችለንን ፍቃድ ባይሰጡንም እንኳን፣ ከእርስዎ IP አድራሻ አንፃር የሚገኙበትን ቦታ ማወቅ እንደምንችል እንዲገነዝቡ እንፈልጋለን፡፡

ክፍል IV – የካሊፎርኒያ እና ሌሎች ስቴቶች ነዋሪዎችን የግላዊነት መብት በተመለከተ  

ከዚህ በታች ያሉት ደንበኞች የካሊፎርኒያ ግዛት እና በሌሎች አንዳንድ ግዛቶች (ማለትም ኮሎራዶ፣ ኮኔክቲከት፣ ኔቫዳ፣ ኡታህ፣ ቨርጂኒያ፣ እንዲሁም በዴላዌር፣ ኢንዲያና፣ አዮዋ፣ ሞንታና፣ ኦሪገን፣ ቴኔሴ እና ቴክሳስ አዲስ ሕግ መሰረት) አካባቢዎች በሚኖሩ ተሳታፊዎች፣ ጎብኚዎች፣ እና ደንበኞች ላይ እንደ አግባቢ ተፈፃሚ የሚሆን ነው፡፡ በሌሎች ግዛቶች ሕጎች ወይም በ California Privacy Rights Act of 2020 (“CPRA”) መሰረት ከጥበቃ ነፃ የተደረጉ የግል መረጃዎችን አይመለከትም፡፡ 

የማወቅ መብት፡  በየጊዜው የምንሰበስበውን የእርስዎን የግል መረጃ አይነቶችን (በህግ መሰረት) የመጠየቅ፣ መረጃውን የሰበሰብንባቸውን ምንጮች አይነት፣ መረጃውን ለመሰብሰብ ወይም ለመሸጥ ያስፈለገበትን ስራ ጉዳይ፣ እንዲሁም የግል መረጃዎን ያካፈልናቸውን ወይም የሸጥንላቸውን ድርጅቶችን አይነት የማወቅ መብት አለዎት፡፡ እንዲሁም ደግሞ ስለ እርስዎ በየጊዜው  የሰበሰብነውን የግል መረጃዎች (በህጉ መሰረት) ኮፒ ወይም ቅጂ የማግኘት መብት አለዎት፡፡ በህግ የተቀመጠው ገደብ እንዳለ ሆኖ፣ የካሊፎርኒያ ነዋሪ ከሆኑ በ 12 ወር ጊዜ ውስጥ እስከ ሁለት ጊዜ መረጃውን የመጠየቅ መብት አለዎት፡፡ ሌሎችም ግዛቶች የተቀመጠ ገደብ አላቸው፡፡ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ የሰበሰብናቸውን እና ያጋራናቸው መረጃዎችን አይነት ማወቅ ከፈለጉ እባክዎ ከላይ የተዘረዘረውን የግላዊነት መመሪያ ክፍል ያንብቡ፡፡ 

የማስተካከል መብት፡ ስለ እርስዎ ያለን የግል መረጃ የተሳሳተ ከሆነ፣ እንድናስተካክል የመጠየቅ መብት አለዎት፡፡ 

መረጃን የማጥፋት ህጉ እንድናስቀምጥ ከሚፈቅድልን ውጪ ያሉትን የግል መረጃዎችዎን ከሲስተማችን ላይ እንድናጠፋቸው የመጠየቅ መብት አለዎት፡፡ ስለ እርስዎ የሰበሰብናቸውን የግል መረጃዎች እንድናጠፋልዎት ጠይቀውን ምላሽ በምንሰጥዎት ጊዜ፣ ምን አይነት የተወሰኑ መረጃዎችን እንደማናጠፋ (የማይጠፋ ካለ ማለት ነው) እና እነዚህን ውስን መረጃዎች የማናጠፋበትን ምክኒያት ጨምረን እናስረዳዎታለን፡፡ ከዚህ በፊት የቀረበው በህግ ነፃ የተደረጉ የግል መረጃዎችን አይመለከትም፡፡  

የተሰበሰበውን መረጃ ለማወቅ ፣ እንዲስተካከል ለመጠየቅ፣ ወይም እንዲጠፋልዎት ለመጠየቅ፡ የትኞቹን መረጃዎችን እንደሰበሰብን፣ የሚስተካከል መረጃ ካለ ለማሳወቅ፣ ወይም ደግሞ እንዲጠፋልዎት ስለሚፈልጉት የግል መረጃ ለመጠየቅ ከፈለጉ እባክዎ ያነጋግሩን በሚለው የአፕሊኬሽኑ የውስጥ መስመር ወይም ደግሞ በዚህ አድራሻ [email protected] ኢሜል ይላኩልን፡፡ ጥያቄውን ሲያቀርቡልን፣ ምላሽ ከመስጠታችን በፊት አስቀድመን ስለ እርስዎ ማንነት እናረጋግጣለን፡፡ ይህን የምናደርገው የእርስዎን መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ ነው፡፡ ከዚያም የኢሜል አድራሻዎን እንዲነግሩን እንጠይቃለን፡፡ የእኛን አገልግሎት ለመጠቀም አካውንት ከፍተው ከነበር፣ አካውንቱን የከፈቱበትን ኢሜል አድራሻ ሊነግሩን ይገባል፡፡   

ለወኪል ፍቃድ ከሰጡ፡  በአንዳንድ የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የእርስዎ ወኪል እርስዎን ወክሎ ጥያቄውን እንዲያቀርብ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ውክልና መስጠትዎን የሚያረጋግጥ መረጃ እንጠይቃለን፡፡ ህጉ የማይከለክለን ከሆነ፣ የወከሉት ሰው እርስዎን የምናነጋግርበትን መረጃ እንዲሰጡን እንጠይቃለን፡፡ ከዚያም የወከሉት ሰው ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ እርስዎን እናነጋግርዎታለን፡፡ ምላሽ ከሰጡን በኋላ በፍጥነት ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ እናስተናግዳለን፡፡  

ያለ እርስዎ ፍቃድ የግል መረጃዎን አንሸጥም፡  የጎብኚዎችን ወይም የደንበኞችን የግል መረጃ አንሸጥም፡፡ በጥናቶቻችን የሚሳተፉ ተሳታፊዎችን የግል መረጃዎች ማለትም ቪዲዮዎች፣ ምስሎች፣ የድምፅ ቅጂዎች፣ ፎቶዎች፣ ስክሪንሾቶች፣ በተሳታፊዎቻችን ፍቃድ መሰረት እና በዚህ የግላዊነት መመሪያ በተገለፀው መልኩ ለሶስተኛ ወገን ልንሸጥ እንችላለን፡፡   

ያለመድሎ መብትን መጠቀም መብትዎን ያለምንም መድሎ የመጠቀም ነፃነት አለዎት፡፡  

የካሊፎርኒያ ነዋሪዎች እኛ ለሶስተኛ ወገን ድርጅቶች ለማርኬቲንግ ዓላማ እንዲጠቀሙበት የሰጠናቸውን መረጃዎች የማወቅ መብት ለማርኬቲን ዓላማዎችን እንዲጠቀሙበት በማለት ምን ዓይነት የግል መረጃዎችን ለሶስተኛ ወገን ድርጅቶች ወይም አጋር ድርጅቶች እንደሰጠን እንድንነግርዎት የመጠየቅ መብት አለዎት፡፡ በዚህ ዙሪያ ጥያቄ ለማቀረ እባክዎ በዚህ አድራሻ [email protected] ኢሜል ይላኩልን፡፡ ለጥያቄዎ መልስ እስከምንሰጥዎት እስከ 30 ቀናት መጠበቅ ሊኖርብዎት ይችላል፡፡ እንዲህ አይነት ጥያቄ በአመት አንድ ጊዜ ማቅረብ ይችላሉ፡፡